La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢዮብ 17:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንግዲህ ተስፋዬ ወዴት ነው? ተስፋዬንስ የሚያይ ማን ነው?

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ታዲያ፣ የእኔ ተስፋ ወዴት ነው? ተስፋዬን የሚያይልኝስ ማን ነው?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ታዲያ፥ እኔ ምን ተስፋ አለኝ? ተስፋ የሚሆነኝንስ ነገር ማን ያይልኛል?

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ግ​ዲህ ተስ​ፋዬ ወዴት ናት? ዳግ​መ​ኛስ መል​ካም ነገ​ርን አያ​ታ​ለ​ሁን?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንግዲህ ተስፋዬ ወዴት ነው? ተስፋዬንስ የሚያይ ማን ነው?

Ver Capítulo



ኢዮብ 17:15
9 Referencias Cruzadas  

እነሆ፥ ሊገድለኝ ይችላል፥ ተስፋም ባይኖረኝ፥ ነገር ግን ስለ መንገዴ በፊቱ እሟገታለሁ።


ውኆች ድንጋዮቹን ይፍቃሉ፥ ፈሳሾቹም የምድሩን አፈር ይወስዳሉ፥ እንዲሁም የሰውን ተስፋ ታጠፋዋለህ።


በዚህና በዚያም አፈረሰኝ፥ እኔም ሄድሁ፥ ተስፋዬንም እንደ ዛፍ ነቀለው፥


አምላክህን መፍራትህ መጽናናትህ፥ የቅንነትህም መንገድ ተስፋህ አይደለምን?


እጠብቅ ዘንድ ጉልበቴ ምንድነው? እታገሥም ዘንድ ፍጻሜዬ ምንድነው?


ቀኖቼ ከሸማኔ መወርወርያ ይልቅ ይቸኩላሉ፥ ያለ ተስፋም ያልቃሉ።”


እኔ፦ በሕይወት ዘመኔ እኩሌታ ከሕይወት ልለይ ይገባልን? በቀረው ዘመኔስ ወደ ሲኦል በሮች መግባት አለብኝን? አልኩ።


እኔም፦ ኃይሌ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ያለው ተስፋዬ ጠፋ አልሁ።


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ አጥንቶች መላው የእስራኤል ቤት ናቸው፤ እነሆ፦ “አጥንቶቻችን ደርቀዋል ተስፋችንም ጠፍቶአል፤ ፈጽመን ተቆርጠናል” ይላሉ።