ኢዮብ 15:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቁጣህን በእግዚአብሔር ላይ እስከ ማንሣት ደርሰህ፥ እነኚህንም ቃላት ከአፍህ እስከ ማውጣት ደርሰህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔር ላይ እንድትቈጣ፣ እንደዚህ ያለ ቃል ከአፍህ እንዲወጣ ያደረገህ ምንድን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም በማድረግህ በእግዚአብሔር ላይ መንፈስህን አነሣሥተሃል። እንዲህ ያለውን ሁሉ የወቀሳ ቃል እስከ መናገር ደርሰሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔር ፊት በቍጣ ትመልስ ዘንድ፤ እንደዚህስ ያለ ነገር ከአፍህ ታወጣ ዘንድ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእግዚአብሔር ላይ መንፈስህን እስከ ማንሣት ደርሰህ፥ ይህንም ቃል ከአፍህ እስከ ማውጣት ደርሰህ። |
ገና ይህን ተናግሮ ሳይጨርስ ንጉሡ ድንገት ከተፍ ብሎ “ይህን መከራ በእኛ ላይ ያመጣብን እግዚአብሔር ነው፤ ታዲያ እርሱ አንድ ነገር ያደርግ ዘንድ ከዚህ በላይ ምን ልጠብቅ?” አለ።
እናንተ ግን፦ የጌታ መንገድ ቀና አይደለም ትላላችሁ። የእስራኤል ቤት ሆይ ስሙ፥ በውኑ መንገዴ ቀና አይደለምን? ቀና ያልሆነውስ የእናንተ መንገድ አይደለምን?