ኤርምያስ 18:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁን እንግዲህ ለይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም ለሚቀመጡ፦ ‘ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ክፉ ነገር እፈጥርባችኋለሁ፥ አሳብንም አስብባችኋለሁ፤ አሁንም ሁላችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፥ መንገዳችሁንና ሥራችሁንም አስተካክሉ’ ብለህ ተናገራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አሁንም እንግዲህ ለይሁዳ ሕዝብና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ እንዲህ በላቸው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ ጥፋትን እያዘጋጀሁላችሁ ነው፤ ክፋትንም እየጠነሰስሁላችሁ ነው። ስለዚህ ሁላችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ መንገዳችሁንና ተግባራችሁን አቅኑ።” ’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም እኔ እነርሱን ለመቅጣት በእነርሱ ላይ ክፉ ነገር የማደርግ መሆኔን ለይሁዳና ለኢየሩሳሌም ሕዝብ ንገራቸው፤ ኃጢአት መሥራትን እንዲተዉና አካሄዳቸውንና አሠራራቸውን ሁሉ እንዲለውጡ ምከራቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁን እንግዲህ ለይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ ክፉ ነገር እፈጥርባችኋለሁ፤ ምክርንም እመክርባችኋለሁ፤ አሁንም ሁላችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ መንገዳችሁንና ሥራችሁንም አቅኑ ብለህ ተናገራቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁን እንግዲህ ለይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም ለሚቀመጡ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ክፉ ነገር እፈጥርባችኋለሁ፥ አሳብንም አስብባችኋለሁ፥ አሁንም ሁላችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፥ መንገዳችሁንና ሥራችሁንም አቅኑ ብለህ ተናገራቸው። |
ሚክያስም “እንግዲህ የተወሰነው ይህ ነው፤ እነዚህን የአንተን ነቢያት የሐሰት ቃል እንዲነግሩህ ያደረጋቸው ጌታ ነው፤ ስለዚህ በአንተ ላይ መዓት ሊያመጣብህ ጌታ ራሱ ወስኖአል!” ሲል ንግግሩን ደመደመ።
እግዚአብሔርም እስራኤልንና ይሁዳን የሚያስጠነቅቁ መልእክተኞችንና ነቢያትን በመላክ “ከክፉ መንገዳችሁ ሁሉ ተመለሱ፤ አገልጋዮቼ በሆኑት ነቢያትና ባለ ራእዮች አማካይነት ለቀድሞ አባቶቻችሁና ለእናንተም በሰጠሁት ሕጎችና ትእዛዞች የተጻፈውን ሥርዓቴን ጠብቁ” ብሎ ነግሮአቸው ነበር።
“እንግዲህ ሂዱና እኔና የይሁዳ ነዋሪ ሕዝብ በዚህ በተገኘው መጽሐፍ ስላለው ትምህርት ማወቅ እንችል ዘንድ እግዚአብሔርን ጠይቁ፤ የቀድሞ አባቶቻችን በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን መመሪያ ስላልተከተሉ እግዚአብሔር በእኛ ላይ በጣም ተቆጥቶአል።”
ንጉሡም “ይህን ደብዳቤ ይዘህ ወደ እስራኤል ንጉሥ ሂድ” ብሎ ፈቀደለት። ስለዚህም ንዕማን ሠላሳ ሺህ ጥሬ ብር፥ ስድስት ሺህ መሐለቅ ወርቅና ምርጥ የሆነ ዐሥር መለወጫ ልብስ አስጭኖ፥ ጉዞውን ቀጠለ፤
እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ እንደ የዋህ በግ ጠቦት ሆንሁ፤ እነርሱም፦ “ዛፉን ከነፍሬው እናጥፋ፥ ስሙም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይታወስ ከሕያዋን ምድር እናስወግደው” ብለው ምክርን እንዳሰቡብኝ አላወቅሁም ነበር።
እነርሱም፦ “ሕግ ከካህን፥ ምክርም ከጠቢብ፥ ቃልም ከነቢይ አይጠፋምና ኑ፥ በኤርምያስ ላይ ሤራን እናሢር። ኑ፥ በአንደበት እንምታው፥ ቃላቱንም ሁሉ አናድምጥ” አሉ።
“የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ቃሌን እንዳይሰሙ አንገታቸውን አደንድነዋልና እነሆ፥ በዚህች ከተማና በመንደሮችዋ ሁሉ ላይ የተናገርሁባትን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣለሁ።”
እንዲህም በል፦ ‘የይሁዳ ነገሥታትና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሆይ! የጌታን ቃል ስሙ፤ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ክፉን ነገር በዚህ ስፍራ ማምጣቴን የሚሰማ ጆሮ ሁሉ ጭው ይልበታል።
እርሱም፦ ሁላችሁ እናንተ ከክፉ መንገዳችሁና ከሥራችሁ ክፋት ተመለሱ፤ ጌታም ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጣችሁ ምድር ተቀመጡ።
እነሆ፦ “ሰው ሚስቱን ቢፈታ፥ ከእርሱም ብትሄድ ሌላም ወንድ ብታገባ፥ በውኑ በድጋሚ ወደ እርሷ ይመለሳልን? ያች ምድር እጅግ የረከሰች አትሆንምን? አንቺ ከብዙ ውሽሞች ጋር አመንዝረሻል፥ ወደ እኔም ትመለሻለሽን? ይላል ጌታ።
እንዲሁም፦ ‘እያንዳንዳችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፥ ሥራችሁንም አሳምሩ፥ ልታገለግሉአቸውም ሌሎችን አማልክት አትከተሉ፥ ለእናንተና ለአባቶቻችሁም በሰጠሁት ምድር ትቀመጣላችሁ’ እያልሁ በማለዳ ተነሥቼ ባርያዎቼን ነቢያትን ሁሉ ላክሁባችሁ፤ ላክሁ፥ እናንተ ግን ጆሮአችሁን አላዘነበላችሁም እኔንም አልሰማችሁኝም።
ምናልባት የይሁዳ ቤት እኔ ላደርግባቸው ያሰብኩትን ክፉ ነገር ሁሉ ይሰሙ ይሆናል፥ ከዚህም የተነሣ ሁላቸውም ከክፉ መንገዳቸው ተመልሰው በደላቸውንና ኃጢአታቸውን ይቅር እል ይሆናል።”
ጌታ በዚህ ሕዝብ ላይ የተናገረው ቁጣውና መዓቱ ታላቅ ነውና ምናልባት ልመናቸው በጌታ ፊት ይቀርብ ይሆናል፥ ሁሉም ከክፉ መንገዱ ይመለስ ይሆናል።”
ፍላጾችን ሳሉ ጋሻዎችንም አንሡ፤ ጌታ ሊያጠፋት አሳቡ በባቢሎን ላይ ነውና የሜዶንን ነገሥታት መንፈስ አስነሥቶአል፤ የጌታ በቀል ስለ መቅደሱ ሲል የሚበቀለው በቀል በእርሷ ላይ ነውና።
ምክንያቱም እኔ ያላሳዘንሁትን የጻድቁን ልብ በውሸት አሳዝናችኋልና፥ ከክፉ መንገዱ ተመልሶ በሕይወትም እንዳይኖር የኃጢአተኛውን እጅ አበርትታችኋልና፤
ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ በዚህ ቤተሰብ ላይ ክፉ አቅጃለሁ፥ ከዚያም አንገታችሁን ማውጣት አትችሉም፤ በትዕቢትም አትሄዱም፥ ጊዜው ክፉ ነውና።
ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ “የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል ወደ እኔ ተመለሱ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።”
ነገር ግን አስቀድሜ በደማስቆ ላሉት በኢየሩሳሌምም በይሁዳም አገር ሁሉ ለአሕዛብም ንስሓ ይገቡ ዘንድና ለንስሓ የሚገባ ነገር እያደረጉ ወደ እግዚአብሔር ይመለሱ ዘንድ ተናገርሁ።
እናንተ “ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህች ወይም ወደዚያች ከተማ እንሄዳለን፤ በእርሷም አንድ ዓመት እንቈያለን፤ እንነግዳለን፤ እናተርፋለንም” የምትሉ ተመልከቱ፤