ኢሳይያስ 58:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሁልጊዜ ይመራሃል፤ ነፍስህንም በመልካም ነገር ያጠግባል አጥንትህንም ያጠናል፤ አንተም እንደሚጠጣ ገነት፥ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሁልጊዜ ይመራሃል፤ ፀሓይ ባቃጠለው ምድር ፍላጎትህን ያሟላል፤ ዐጥንትህን ያበረታል፤ በውሃ እንደ ረካ የአትክልት ቦታ፣ እንደማይቋርጥም ምንጭ ትሆናለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ሁልጊዜ እመራችኋለሁ፤ በድርቅም ቦታ ፍላጎታችሁን አረካለሁ፤ አጥንታችሁንም አጠነክራለሁ፤ ውሃ እንደሚጠጣ የአትክልት ቦታና ደርቆ እንደማያውቅ ምንጭ ትሆናላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሁልጊዜ ከአንተ ጋር ይኖራል፤ እንደ ነፍስህም ፍላጎት ያጠግብሃል፤ አጥንትህንም ያለመልማል፤ አንተም እንደሚጠጣ ገነት፥ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሁል ጊዜ ይመራሃል፥ ነፍስህንም በመልካም ነገር ያጠግባል አጥንትህንም ያጠናል፥ አንተም እንደሚጠጣ ገነት፥ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ። |
እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለ፥ ፍሬውን በየጊዜው እንደሚሰጥ፥ ቅጠሉም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፥ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።
ታያላችሁ፥ ልባችሁም ሐሤት ታደርጋለች፥ አጥንታችሁም እንደ ለምለም ሣር ትበቅላለች፤ የጌታም እጅ ለሚፈሩት ትታወቃለች፥ በጠላቶቹም ላይ ይቈጣል።
በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለ፥ በወንዝም ዳር ሥሮቹን እንደሚዘረጋ፥ ሙቀትም በመጣ ጊዜ እንደማይፈራ፥ ቅጠሉም እንደሚለመልም፥ በድርቅ ዓመትም እንደማይሠጋ ፍሬውንም ከማፍራት እንደማያቋርጥ ዛፍ ይሆናል።”
ይመጣሉ በጽዮንም ተራራ ላይ ሆነው እልል ይላሉ፤ ስለ ጌታም በጎነቱ፥ ስለ እህሉና ስለ ወይን ጠጁ፥ ስለ ዘይቱም፥ ስለ በጎቹና ስለ ከብቶቹ በሐሤት ይሞላሉ፤ ነፍሳቸውም ውኃ ጠጥታ እንደ ረካች ገነት ትሆናለች፥ ከእንግዲህም ወዲህ አያዝኑም።
“ባድማ የነበረች ይህች ምድር እንደ ዔድን ገነት ሆነች፤ የወደሙት፥ ባድማ የሆኑት፥ የፈረሱት ከተሞች አጥር ተሰርቶላቸዋል፥ መኖሪያም ሆነዋል” ይላሉ።
የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ግን እርሱ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ ከራሱ አይናገርምና፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።
እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘለዓለም አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውሃ በእርሱ ውስጥ ለዘለዓለም ሕይወት የሚፈልቅ የውሃ ምንጭ ይሆናል እንጂ፤” አላት።