እነርሱም በእጃቸው ያሉትን ባዕዳን አማልክት ሁሉ፥ እንዲሁም በጆሮአቸውም ያሉትን ጉትቾች ለያዕቆብ ሰጡት፥ ያዕቆብም በሴኬም አጠገብ ካለችው የባሉጥ ዛፍ በታች ቀበራቸው።
ኢሳይያስ 2:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ቀን ሰዎች ሊያመልኳቸው ያበጇቸውን፤ የብርና የወርቅ ጣዖቶቻቸውን ለፍልፈልና ለሌሊት ወፍ ይወረውራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ቀን ሰዎች ሊያመልኳቸው ያበጇቸውን፣ የብርና የወርቅ ጣዖቶቻቸውን ለፍልፈልና ለሌሊት ወፍ ይወረውራሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎች ይሰግዱላቸው ዘንድ በእጃቸው የሠሩአቸውን የብርና የወርቅ ምስሎች ለፍልፈሎችና ለሌሊት ወፎች እየጣሉላቸው ይሄዳሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን ሰው ይሰግድላቸው ዘንድ ያበጁአቸውን የብሩንና የወርቁን ጣዖቶቹን ለፍልፈልና ለሌሊት ወፍ ይጥላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ቀን ሰው ይሰግድላቸው ዘንድ ያበጁአቸውን የብሩንና የወርቁን ጣዖቶቹን ለፍልፈልና ለሌሊት ወፍ ይጥላል። |
እነርሱም በእጃቸው ያሉትን ባዕዳን አማልክት ሁሉ፥ እንዲሁም በጆሮአቸውም ያሉትን ጉትቾች ለያዕቆብ ሰጡት፥ ያዕቆብም በሴኬም አጠገብ ካለችው የባሉጥ ዛፍ በታች ቀበራቸው።
በምትጎበኙበት ቀን ምን ይውጣችኋል? ጥፋት ከሩቅ ሲመጣስ ምን ትሆናላችሁ? ርዳታን ለማግኘትስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ሀብታችሁንስ የት ታገኙታላችሁ?
በብርም የተለበጡትን የተቀረጹትን ምስሎችህን፥ በወርቅም የተለበጡትን ቀልጠው የተሠሩትን ምስሎችህን ታረክሳለህ፤ እንደ ርኩስም ነገር ትጥላቸዋለህ፦ “ከእኔ ራቁ!” ትላቸዋለህ።
ወርቁን ከኮሮጆ የሚያፈስሱ፥ ብሩንም በሚዛን የሚመዝኑ እነርሱ አንጥረኛውን ይቀጥራሉ፤ እርሱም አምላክ አድርጎ ይሠራዋል፤ ለዚያም ይጐነበሱለታል ይሰግዱለትማል።
ስለዚህ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመለሱ፥ ከጣዖቶቻችሁም ተመለሱ፥ ከርኩሰቶቻችሁ ሁሉ ፊታችሁን መልሱ።
ብራቸውን በጎዳናዎቹ ላይ ይጥላሉ፥ ወርቃቸውም እንደ ርኩስ ነገር ይቆጠራል፥ በጌታ የመዓት ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም። አይጠግቡም፥ ሆዳቸውንም አይሞሉም፥ የኃጢአታቸው ዕንቅፋት ሆኖአልና።
ከጥላውም በታች የሚቀመጡ ይመለሳሉ፤ እንደ አትክልት ስፍራ ይለመልማሉ፤ እንደ ወይንም ተክል ያብባሉ፤ መዓዛቸውም እንደ ሊባኖስ ወይን ጠጅ ይሆናል።
ጌታ በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፥ የምድርን አማልክት ሁሉ ያጠፋቸዋልና፤ የሕዝቦችም ደሴቶች ሁሉ ላይ የሚኖሩ ሰዎች፥ ሁሉም በያሉበት ሆነው ለእርሱ ይሰግዳሉ።