ታዲያ በገዛ ቤቱ፥ በገዛ አልጋው ላይ ዐርፎ የተኛውን ንጹሕ ሰው የገደሉትን ክፉ ሰዎች እንዴት የባሰ ቅጣት አይገባቸውም? ደሙን ከእጃችሁ መፈለግ፥ እናንተን ከምድሪቱ ማጥፋት የለብኝምን?”
ዕብራውያን 9:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበው የክርስቶስ ደም እንዴት ልቆ፥ ሕያው እግዚአብሔርን ለማምለክ፥ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን! አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዘላለም መንፈስ አማካይነት ራሱን ነውር አልባ መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ያቀረበው የክርስቶስ ደም፣ ሕያው እግዚአብሔርን እንድናመልክ ኅሊናችንን ከምውት ሥራ እንዴት ይበልጥ ያነጻ ይሆን! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዘለዓለም መንፈስ አማካይነት ራሱን ነውር የሌለበት መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ያቀረበው የክርስቶስ ደም ሕያው እግዚአብሔርን እንድናገለግል ኅሊናችንን ከሞተ ሥራ እንዴት ይበልጥ ያነጻ ይሆን! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነውር የሌለው ሆኖ፥ በዘለዓለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም ሕያው እግዚአብሔርን እናመልከው ዘንድ ሕሊናችንን ከሞት ሥራ እንዴት ይልቅ ያነጻ ይሆን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን? |
ታዲያ በገዛ ቤቱ፥ በገዛ አልጋው ላይ ዐርፎ የተኛውን ንጹሕ ሰው የገደሉትን ክፉ ሰዎች እንዴት የባሰ ቅጣት አይገባቸውም? ደሙን ከእጃችሁ መፈለግ፥ እናንተን ከምድሪቱ ማጥፋት የለብኝምን?”
አሁንም እግዚአብሔር ሆይ፤ የደረሰብንን ነገር ሁሉ ተመልከት፥ ሕያው አምላክን አንተን በመስደብ ሰናክሬም የተናገረውን የዛቻ ቃል ሁሉ አድምጥ፤
ለዘለዓለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ፥ ከፍ ያለው ልዑል እንዲህ ይላል፦ የተዋረዱትን ሰዎች መንፈስ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠውንም ልብ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠና የተዋረደ መንፈስ ካለው ጋር በከፍታና በተቀደሰ ስፍራ እቀመጣለሁ።
የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ ጌታ ቀብቶኛልና፥ ልባቸው የተሰበረውን እንድጠግን፥ ለተማረኩትም ነጻነትን፥ ለታሰሩትም መፈታትን እንዳውጅ ልኮኛል።
ጌታ ግን እውነተኛ አምላክ ነው፤ እርሱም ሕያው አምላክና የዘለዓለም ንጉሥ ነው፤ ከቁጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች፤ አሕዛብም መዓቱን መቋቋም አይችሉም።
“በወሩም መባቻ ለጌታ የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርቡ፤ ሁለት ወይፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ ነውርም የሌለባቸውን ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ታቀርባላችሁ፤
እንዲህም በላቸው፦ ‘ለጌታ በእሳት የምታቀርቡት ቁርባን ይህ ነው፤ ለዘወትር ለሚቃጠል መሥዋዕት ነውር የሌለባቸውን ሁለት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ዕለት ዕለት ታቀርባላችሁ።
“በሰንበትም ቀን ነውር የሌለባቸውን ሁለት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፥ ለእህልም ቁርባን በዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ መልካም ዱቄት፥ የመጠጡንም ቁርባን ታቀርባላችሁ።
እንግዲህ እናንተ ክፉዎች ሆናችሁ ሳለ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁማ ለሚለምኑት መልካም ነገርን እንዴት አብልጦ አይሰጣቸውም!
ቁራዎችን ተመልከቱ፤ አይዘሩም፤ አያጭዱምም፤ ዕቃ ቤትም ወይም ጎተራ የላቸውም፤ እግዚአብሔርም ይመግባቸዋል፤ እናንተማ ከወፎች እጅግ ትበልጡ የለምን?
እግዚአብሔር ግን ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን በሜዳ የሆነውን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፥ እናንተ እምነት የጐደላችሁ፥ እናንተንማ ይልቁን እንዴት?
“የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድሆች መልካም ዜናን እንዳበሥር ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዐይነ ስውሮችም ማየትን እንዳውጅ፥ የተጨቆኑትንም ነጻ እንዳወጣ
እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፤ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፤ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤
እንዲህም አሉ “እናንተ ሰዎች! ይህን ስለምን ታደርጋላችሁ? እኛ ደግሞ እንደ እናንተ የምንሰማ ሰዎች ነን፤ ከዚህም ከንቱ ነገር ሰማይንና ምድርን ባሕርንም በእርነርሱም ያለውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ትመለሱ ዘንድ ወንጌልን እንሰብካለን።
አንተ በተፈጥሮ የበረሃ ከነበረ የወይራ ዛፍ ተቆርጠህ እንደ አፈጣጠርህ ሳትሆን በመልካም የወይራ ዛፍ ከገባህ፥ ይልቁንስ እነዚያ በተፈጥሮአቸው ቅርንጫፎች የሆኑት በራሳቸው የወይራ ዛፍ እንዴት አይገቡም?
የሰውነታችሁን ክፍሎች የክፋት መሣሪያ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ፤ ነገር ግን ከሙታን ተለይታችሁ እንደምትኖሩ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፤ የሰውነታችሁንም ክፍሎች የጽድቅ መሣሪያ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።
የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከጣዖት ጋር ምን ስምምነት አለው? እኛ እኮ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን፤ እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ተናግሯል፥ በእነርሱ እኖራለሁ፤ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።
ክርስቶስም እንዳፈቀራችሁ፥ ስለ እናንተም ለእግዚአብሔር መልካም መዓዛ ያለው መባንና መሥዋዕት አድርጎ ራሱን አሳልፎ እንደሰጠ፥ በፍቅር ተመላለሱ።
አንድ እንስሳ እንከን ያለው፥ አንካሳ ወይም ዕውር፥ ወይም ደግሞ ማናቸውም ዓይነት ከባድ ጉድለት ያለበት ከሆነ ለጌታ ለእግዚአብሔር አትሠዋው፤
እኔ ዓመፃችሁንና የአንገታችሁን ድንዳኔ አውቃለሁና፥ እኔም ዛሬ ከእናንተ ጋር ገና በሕይወት ሳለሁ እናንተ በጌታ ላይ ዐምፃችኋል፥ ይልቁንስ ከሞትሁ በኋላ እንዴት ይሆናል?
እነርሱ ራሳቸው ስለ እኛ በእናንተ መካከል ምን ዓይነት አቀባበል ተደርጎልን እንደ ነበር፥ ሕያውም የሆነውን እውነተኛ አምላክ ለማገልገል ከጣዖታት ወደ እግዚአብሔር እንዴት እንደተመለሳችሁ፥
ይህ ሳይሆን ቀርቶ ብዘገይ ግን፥ በዚህ በጻፍሁልህ ትእዛዝ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ የእውነት ዓምድና መሠረት በሆነችው በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ እንድታውቅ ነው።
መድኃኒታችንም ከኃጢአት ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።
ስለዚህ የክርስቶስን የመጀመሪያ ትምህርት አልፈን ወደ ፍጻሜ እንሂድ፤ መሠረትን ደግመን አንመሥርት፤ እርሱም ከሞተ ሥራ ንስሓና በእግዚአብሔር እምነት፥
እርሱ እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት፥ አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት፥ ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ማቅረብ አያስፈልገውም፤ ይህን ራሱን ባቀረበ ጊዜ አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎታል።
እንዲህ ቢሆን ኖሮ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ መከራ ሊቀበል ባስፈለገው ነበር፤ አሁን ግን በዓለም ፍጻሜ ራሱን በመሠዋት ኃጢአትን ሊሽር አንድ ጊዜ ተገልጦአል።
በሁለተኛይቱ ግን ሊቀ ካህናት ብቻውን በዓመት አንድ ጊዜ ይገባባታል፤ እርሱም ሰለ ራሱና ስለ ሕዝቡ ኃጢአት የሚያቀርበውን ደም ሳይዝ አይገባም፤
ክርስቶስ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዐመፀኞች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ስለ ኃጢአት መከራን ተቀበለ፤ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ሊያቀርባችሁ በሥጋ ሞተ፥ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ።
ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ እርስ በእርሳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።
እንዲሁም ከታመነው ምስክር፥ ከሙታን በኩር ከሆነው፥ የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ፤ ለወደደን፥ ከኀጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥
ዳዊት በአጠገቡ የቆሙትን ሰዎች፥ “ይህን ፍልስጥኤማዊ ገድሎ እንዲህ ያለውን ውርደት ከእስራኤል ለሚያስወግድ ሰው ምን ይደረግለታል? ደግሞስ የሕያው እግዚአብሔርን ሠራዊት ይገዳደር ዘንድ ይህ ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ እርሱ ማነው?” ሲል ጠየቀ።