2 ሳሙኤል 4:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም እናንተ ክፉዎች ሰዎች በቤቱ ውስጥ በአልጋው ላይ ጻድቁን ሰው ገደላችሁት፤ እነሆ፥ ደሙን ከእጃችሁ እሻለሁ፤ ከምድርም አጠፋችኋለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታዲያ በገዛ ቤቱ፣ በገዛ ዐልጋው ላይ ዐርፎ የተኛውን ንጹሕ ሰው የገደሉትን ክፉ ሰዎች እንዴት የባሰ ቅጣት አይገባቸውም? ደሙን ከእጃችሁ መፈለግ፣ እናንተን ከምድሪቱ ማጥፋት የለብኝምን?” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታዲያ በገዛ ቤቱ፥ በገዛ አልጋው ላይ ዐርፎ የተኛውን ንጹሕ ሰው የገደሉትን ክፉ ሰዎች እንዴት የባሰ ቅጣት አይገባቸውም? ደሙን ከእጃችሁ መፈለግ፥ እናንተን ከምድሪቱ ማጥፋት የለብኝምን?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ፥ በገዛ ቤቱ ተኝቶ የነበረውን ንጹሕ ሰው ለገደሉት ሰዎችማ የሚከፈላቸው የበቀል ዋጋ ምን ያኽል የከፋ ይሆን? ስለዚህም እርሱን በመግደላችሁ ምክንያት እኔ በእናንተ ላይ የበቀል እርምጃ በመውሰድ ከምድር ላይ ጠራርጌ አጠፋችኋለሁ!” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይልቁንስ በቤቱ ውስጥ በምንጣፋ ላይ ንጹሑን ሰው የገደላችሁትን እናንተን ኃጢአተኞችንማ እንዴት ነዋ? ደሙን ከእጃችሁ አልሻውምን? ከምድርም አላጠፋችሁምን? |
እግዚአብሔር አምላክም ኖኅን አለው፥ “የሰው ሁሉ ጊዜው በፊቴ ደርሶአል፤ ከእነርሱ የተነሣ ምድር በግፍ ተመልታለችና፤ እኔም እነሆ፥ ከምድር ጋር አጠፋቸዋለሁ።
በምድር ላይ የነበረውም ሁሉ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ፥ እስከሚርመሰመሰውም ሁሉ ድረስ፥ እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ ተደመሰሰ፤ ከምድርም ተደመሰሱ። ኖኅም አብረውት በመርከብ ከነበሩት ጋር ብቻውን ቀረ።
በፋንታው ነግሠሃልና እግዚአብሔር የሳኦልን ቤት ደም ሁሉ መለሰብህ፤ እግዚአብሔርም መንግሥትህን ለልጅህ ለአቤሴሎም እጅ አሳልፎ ሰጥቶታል፤ እነሆም፥ አንተ የደም ሰው ነህና በመከራ ተይዘሃል።”
አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ ኢዮአብ በበር ውስጥ በቈይታ ይናገረው ዘንድ ወደ አጠገቡ ወሰደው፤ በዚያም ለወንድሙ ለአሣሄል ደም ተበቅሎ ወገቡን መታው፤ ሞተም።
እኔም ዛሬ ዘመዱ እንደ ሆንሁ፥ እርሱም በንጉሡ ዘንድ የተሾመ እንደ ሆነ አታውቁምን? እነዚህም ሰዎች የሦርህያ ልጆች በርትተውብኛል፤ እግዚአብሔርም ክፋት በሠራ ላይ እንደ ክፋቱ ይመልስበት” አላቸው።
አባቴ ዳዊት ሳያውቅ ከእርሱ የሚሻሉትን ሁለቱን ጻድቃን ሰዎች፥ የእስራኤልን ሠራዊት አለቃ የኔርን ልጅ አበኔርን፥ የይሁዳንም ሠራዊት አለቃ የኢያቴርን ልጅ አሜሳይን በሰይፍ ገድሎአልና እግዚአብሔር የዐመፅ ደሙን በራሱ ላይ መለሰ።
እናንተም፦ ሰማይንና ምድርን ያልፈጠሩ እነዚህ አማልክት ከምድር ላይ፥ ከሰማይም በታች ፈጽመው ይጥፉ ትሉአቸዋላችሁ።
አቤቱ፥ የተቀደስህ አምላኬ ሆይ፥ አንተ ከዘላለም ጀምሮ አልነበርህምን? እኛ አንሞትም፣ አቤቱ፥ ለፍርድ ሠርተኸዋል፥ ለተግሣጽም አድርገኸዋል።
ከክፉው እንደ ነበረ ወንድሙንም እንደ ገደለ እንደ ቃየል አይደለም፤ ስለ ምንስ ገደለው? የገዛ ሥራው ክፉ፥ የወንድሙም ሥራ ጽድቅ ስለ ነበረ ነው።