2 ሳሙኤል 4:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 መልካም ወሬ የያዘ መስሎት እነሆ፥ ሳኦል ሞተ ብሎ የነገረኝን የምስራቹ ዋጋ እንዲሆን ይዤ በሴቄላቅ ገደልሁት። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 የምሥራች ያመጣልኝ መስሎት፣ ‘እነሆ ሳኦል ሞተ’ ብሎ የነገረኝን ሰው ይዤ ጺቅላግ ላይ ገደልሁት፤ እንግዲህ ለዚያ ሰው ስላመጣው ምሥራች የሸለምሁት ይህን ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 የምሥራች ያመጣልኝ መስሎት፥ ‘ሳኦል ሞተ’ ብሎ የነገረኝን ሰው ይዤ ጺቅላግ ላይ ገደልሁት፤ ለዚያ ሰው ስላመጣው ምሥራች የሸለምሁት ይህን ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 በጺቅላግ ወደ እኔ መጥቶ ስለ ሳኦል ሞት የነገረኝ መልእክተኛም እንደዚሁ መልካም ዜና ያመጣልኝ መስሎት ነበር፤ እኔ ግን እርሱን ይዤ አስገደልኩት፤ መልካም ዜና ነው ብሎ ላመጣውም ወሬ የከፈልኩት ዋጋ ይኸው ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 መልካም ወሬ የያዘ መስሎት፦ እነሆ፥ ሳኦል ሞተ ብሎ የነገረኝን የምስራቹ ዋጋ እንዲሆን ይዤ በጺቅላግ ገደልሁት። ምዕራፉን ተመልከት |