Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 3:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 አበ​ኔ​ርም ወደ ኬብ​ሮን በተ​መ​ለሰ ጊዜ ኢዮ​አብ በበር ውስጥ በቈ​ይታ ይና​ገ​ረው ዘንድ ወደ አጠ​ገቡ ወሰ​ደው፤ በዚ​ያም ለወ​ን​ድሙ ለአ​ሣ​ሄል ደም ተበ​ቅሎ ወገ​ቡን መታው፤ ሞተም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 አበኔር ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ፣ ኢዮአብ በቈይታ የሚያነጋግረው በመምሰል ዞር አድርጎ ወደ ቅጽሩ በር ይዞት ሄደ፤ እዚያም የወንድሙን የአሣሄልን ደም ለመበቀል ሲል፣ ሆዱ ላይ ወግቶ ገደለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ፥ ኢዮአብ ለብቻው የሚያነጋግረው በመምሰል ወደ ቅጽሩ በር ይዞት ሄደ፤ እዚያም የወንድሙን የአሣሄልን ደም ለመበቀል ሆዱ ላይ ወግቶ ገደለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 አበኔር ወደ ኬብሮን በደረሰ ጊዜ ኢዮአብ በግል ሊያነጋግረው የፈለገ በመምሰል ወደ ቅጽሩ በር ገለል አድርጎ ወሰደው፤ እዚያም ሆዱን ወግቶ ገደለው፤ ኢዮአብ ይህን ያደረገበት ምክንያት አበኔር ቀደም ብሎ ወንድሙን ዐሣሄልን ስለ ገደለበት ለመበቀል ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ ኢዮአብ በበር ውስጥ በቆይታ ይናገረው ዘንድ ወደ አጠገቡ ወሰደው፥ በዚያም ለወንድሙ ለአሣሄል ደም ተበቅሎ ሆዱን መታው፥ ሞተም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 3:27
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤ​ሴ​ሎ​ምም፥ “አንተ እንቢ ካልህ ወን​ድሜ አም​ኖን ከእኛ ጋር እን​ዲ​ሄድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለ። ንጉ​ሡም፥ “ከአ​ንተ ጋር ለምን ይሄ​ዳል?” አለው።


ለአ​ሚ​ሳ​ይም፦ አንተ የአ​ጥ​ንቴ ፍላ​ጭና የሥ​ጋዬ ቍራጭ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን? በዘ​መ​ን​ህም ሁሉ በኢ​ዮ​አብ ፋንታ በፊቴ የሠ​ራ​ዊት አለቃ ሳት​ሆን ብት​ቀር ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ያድ​ር​ግ​ብኝ፤ ይህ​ንም ይጨ​ም​ር​ብኝ በሉት።”


ኢዮ​አ​ብም ከዳ​ዊት በወጣ ጊዜ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ከአ​በ​ኔር በኋላ ላከ፤ ከሴ​ይ​ርም ጕድ​ጓድ መለ​ሱት። ዳዊት ግን ይህን አላ​ወ​ቀም።


ከዚ​ህም በኋላ ዳዊት ሰማ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ከኔር ልጅ ከአ​በ​ኔር ደም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እኔ ንጹሕ ነኝ፤ መን​ግ​ሥ​ቴም ንጹሕ ነው፤


የሳ​ኦ​ልም ልጅ ኢያ​ቡ​ስቴ አበ​ኔር በኬ​ብ​ሮን እንደ ሞተ ሰማ፤ እጆ​ቹም ደከሙ፤ እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያ​ንም ሁሉ ደነ​ገጡ።


አባቴ ዳዊት ሳያ​ውቅ ከእ​ርሱ የሚ​ሻ​ሉ​ትን ሁለ​ቱን ጻድ​ቃን ሰዎች፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሠራ​ዊት አለቃ የኔ​ርን ልጅ አበ​ኔ​ርን፥ የይ​ሁ​ዳ​ንም ሠራ​ዊት አለቃ የኢ​ያ​ቴ​ርን ልጅ አሜ​ሳ​ይን በሰ​ይፍ ገድ​ሎ​አ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዐ​መፅ ደሙን በራሱ ላይ መለሰ።


አን​ተም ደግሞ የሶ​ር​ህያ ልጅ ኢዮ​አብ፥ ሁለ​ቱን የእ​ስ​ራ​ኤል ሠራ​ዊት አለ​ቆች የኔር ልጅ አበ​ኔ​ርን የኢ​ያ​ቴ​ር​ንም ልጅ አሜ​ሳ​ይን ገድሎ፥ በእኔ ላይ ያደ​ረ​ገ​ውን ታው​ቃ​ለህ፤ የጦ​ር​ነ​ት​ንም ደም በሰ​ላም አፈ​ሰሰ፤ በወ​ገ​ቡም ባለው ድግና በእ​ግ​ሩም ባለው ጫማ ንጹሕ ደም አኖረ።


በገ​ለ​ዓድ ምድር ባለው በም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ ላይ የዘ​ብ​ድ​ያስ ልጅ ኢዮ​ዳኢ፤ በብ​ን​ያ​ምም ልጆች ላይ የአ​በ​ኔር ልጅ አሳ​ሄል፤


የና​ታ​ን​ያም ልጅ እስ​ማ​ኤል ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት ዐሥሩ ሰዎች ተነ​ሥ​ተው የሳ​ፋ​ንን ልጅ የአ​ኪ​ቃ​ምን ልጅ ጎዶ​ል​ያ​ስን በሰ​ይፍ መቱ፤ የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ በሀ​ገሩ ላይ የሾ​መ​ውን ገደሉ።


ደም ተበ​ቃዩ ራሱ ነፍሰ ገዳ​ዩን ይግ​ደል፤ ባገ​ኘው ጊዜ ይግ​ደ​ለው።


ጥል ቢጣ​ላው፥ ወይም ሸምቆ አን​ዳች ነገር ቢጥ​ል​በት፥ ቢሞ​ትም፥


“ባል​ን​ጀ​ራ​ውን በተ​ን​ኰል የሚ​መታ ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች