La Biblia Online

Anuncios

Toda la Biblia A.T. N.T.


መጽሐፈ ጥበብ 5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
መጽሐፈ ጥበብ 5

1 ያን​ጊዜ ጻድቁ፦ መከራ ባጸ​ኑ​በ​ትና ድካ​ሙን በካዱ፥ ነገ​ሩ​ንም በናቁ ሰዎች ፊት በብዙ መገ​ለጥ ይቆ​ማል።

2 በግ​ር​ማና በክፉ ማስ​ፈ​ራ​ራት ሆኖ ባዩት ጊዜ ይታ​ወ​ካሉ፤ ድንቅ ስለ​ሚ​ሆን ደኅ​ን​ነ​ቱም ይደ​ነ​ቃሉ።

3 እየ​ተ​ጸ​ጸ​ቱና በተ​ጨ​ነቀ መን​ፈስ እየ​ጮኹ እርስ በር​ሳ​ቸው ይና​ገ​ራሉ፦ እን​ዲ​ህም ይላሉ፥ “ቀድሞ በኛ በሰ​ነ​ፎች ዘንድ መሣ​ቂ​ያና ማሽ​ሟ​ጠጫ የሆ​ነው፥

4 ሥራ​ውን ስን​ፍና፥ ሞቱ​ንም የተ​ናቀ ያደ​ረ​ግ​ን​በት ይህ ነውን?

5 እን​ዴት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ሆነ? ርስ​ቱስ እን​ዴት ለቅ​ዱ​ሳን ሆነች?

6 ስለ​ዚህ ከቀና መን​ገድ ወጥ​ተን ስተ​ናል፥ የጽ​ድቅ ብር​ሃ​ንም አል​ተ​ገ​ለ​ጠ​ል​ንም፥ ፀሐ​ይም አል​ወ​ጣ​ል​ንም።

7 በደ​ል​ንና ጥፋ​ትን በመ​ን​ገ​ዳ​ችን ሞላን፤ በም​ድረ በዳም ሄድን፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መን​ገድ አላ​ወ​ቅ​ንም።

8 “ትዕ​ቢት ምን ጠቀ​መን? ከት​ዕ​ቢት ጋር ያለ ባለ​ጠ​ግ​ነ​ትስ ምን አመ​ጣ​ልን?

9 ይህ ሁሉ እንደ ጥላ ኀላፊ ነው፤ ፈጥ​ኖም እን​ደ​ሚ​ሄድ ወሬ ነው።

10 በባ​ሕር ላይ እን​ደ​ሚ​ሄድ፥ ውኃም በማ​ዕ​በሉ እን​ደ​ሚ​ነ​ጥ​ቀው፥ ያለ​ፈ​በት ፍለ​ጋው እን​ደ​ማ​ይ​ገኝ፥ በማ​ዕ​በ​ሉም መካ​ከል አካሉ የሄ​ደ​በት መን​ገድ እን​ደ​ማ​ይ​ታ​ወቅ መር​ከብ፥

11 በአ​የር ላይ የሚ​በ​ርር ዎፍ የሄ​ደ​በት ፍለ​ጋው እን​ደ​ማ​ይ​ገኝ፥ በበ​ረረ ጊዜ ቀላ​ሉን አየር እየ​ከ​ፈለ ፈጥኖ ይሄ​ዳ​ልና፥ ክን​ፉ​ንም እያ​ር​ገ​በ​ገበ፥ ፈጥኖ ይበ​ር​ራ​ልና ከሄ​ደም በኋላ በነ​ፋሱ ውስጥ ያለ​ፈ​በት ምል​ክቱ እን​ደ​ማ​ይ​ገኝ፥

12 ይህም ባይ​ሆን የተ​ወ​ረ​ወረ ፍላፃ ሰን​ጥ​ቆት ያለ​ፈው አየር ተመ​ልሶ እን​ደ​ሚ​ገ​ጥም፥ በአ​የር ውስጥ የሄ​ደ​በ​ትም እን​ደ​ማ​ይ​ታ​ወቅ፥

13 እኛም እን​ዲሁ ነን፤ በተ​ወ​ለ​ድን ጊዜ ጠፋን። በክ​ፋ​ታ​ችን ጠፋን እንጂ በጎ ምል​ክ​ትን እና​ሳይ ዘንድ አል​ተ​ገ​ባ​ንም።”

14 የክ​ፉ​ዎች ሰዎች ተስ​ፋ​ቸው ነፋስ እን​ደ​ሚ​በ​ት​ነው ትቢያ፥ በነ​ፋስ ቀልጦ እን​ደ​ሚ​ጠፋ ረቂቅ ውርጭ፥ በነ​ፋ​ስም ተበ​ትኖ እን​ደ​ሚ​ጠፋ ጢስ፥ አንድ ቀንም አድሮ እን​ደ​ሚ​ሄድ መጻ​ተኛ ስም አጠ​ራር ነው።

ጻድ​ቃን የሚ​ያ​ገ​ኙ​ት​ዋጋ

15 ጻድ​ቃን ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራሉ፤ ዋጋ​ቸ​ውም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የጸና ነው፤ ጥበ​ቃ​ቸ​ውም በል​ዑል ዘንድ ነው።

16 ስለ​ዚ​ህም የክ​ብር መን​ግ​ሥ​ት​ንና ጌጥ ያለው አክ​ሊ​ልን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ይቀ​በ​ላሉ፤ በቀኙ ይሰ​ው​ራ​ቸ​ዋ​ልና፥ በክ​ን​ዱም ይረ​ዳ​ቸ​ዋ​ልና።

17 ፍጹም የሆነ የቅ​ን​ዐ​ቱን ጦር መሣ​ሪያ ይይ​ዛል፤ ጠላ​ቶ​ቹ​ንም ለመ​በ​ቀል ፍጥ​ረ​ቱን የጦር መሣ​ሪያ ያደ​ር​ጋ​ታል።

18 የጽ​ድቅ ጥሩ​ር​ንም ይለ​ብ​ሳል፥ ማድ​ላት የሌ​ለ​በት የፍ​ርድ ራስ ቍር​ንም ይቀ​ዳ​ጃል።

19 የማ​ይ​ሸ​ነፍ የእ​ው​ነት ጋሻ​ንም ይይ​ዛል።

20 መዓ​ቱ​ንም እን​ደ​ሚ​ቈ​ርጥ ሰይፍ ይስ​ላል፤ ዓለ​ምም ከእ​ርሱ ጋር ሆኖ አላ​ዋ​ቂ​ዎ​ችን ይዋ​ጋል።

21 ፈጥኖ ያገ​ኛ​ቸው ዘንድ በአ​ሳ​ቾች ሰዎች ላይ የመ​ብ​ረ​ቆቹ ድል ነጎድ በቀ​ጥታ ይሄ​ድ​ባ​ቸ​ዋል። መል​ካም ሆኖ ከተ​ገ​ተረ ቀስት እን​ደ​ሚ​ወ​ረ​ወር ፍላጻ ከደ​መ​ና​ዎች ውስጥ ወደ ዓላ​ማ​ቸው ይወ​ረ​ወ​ራሉ ።

22 ከመ​ዓቱ ድል ነጎድ ደን​ጊ​ያም ፈጥኖ በረ​ዶን ያወ​ር​ዳል፤ የባ​ሕ​ሩም ውኃ በእ​ነ​ርሱ ላይ ይበ​ሳ​ጭ​ባ​ቸ​ዋል፤ ፈሳ​ሾ​ችም ይነ​ዋ​ወ​ጣሉ፤ ፈጥ​ነ​ውም ይከ​ቧ​ቸ​ዋል።

23 ኀይል ያለው ነፋ​ስም ይቃ​ወ​ማ​ቸ​ዋል፤ እንደ ነፋ​ስም ያደ​ር​ቃ​ቸ​ዋል፤ ኀጢ​አት ምድ​ሩን ሁሉ ታጠ​ፋ​ለ​ችና፥ ክፉም መሥ​ራት የኀ​ያ​ላ​ኑን ዙፋን ይገ​ለ​ብ​ጣ​ልና ይበ​ት​ና​ቸ​ዋል።