ሶፎንያስ 3:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መዓቴንና የቍጣዬን ትኵሳት ሁሉ አፈስስባቸው ዘንድ ፍርዴ አሕዛብን ለመሰብሰብ፥ መንግሥታትንም ለማከማቸት ነውና፥ ምድርም ሁሉ በቅንዓቴ እሳት ትበላለችና ስለዚህ ለመበዝበዝ እስከምነሣበት ቀን ድረስ ጠብቁኝ፥ ይላል እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለዚህ እስከምፈርድበት ቀን ድረስ ጠብቁኝ፤ አሕዛብን ላከማች፣ መንግሥታትን ልሰበስብ፣ መዓቴንና ጽኑ ቍጣዬን በላያቸው ላፈስስ ወስኛለሁ። በቅናቴ ቍጣ እሳት፣ መላዋ ምድር ትቃጠላለችና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ “ጠብቁኝ” ይላል ጌታ፤ ለመበዝበዝ እስከምነሣበት ቀን ድረስ፥ ፍርዴ ሕዝቦችን ለመሰብሰብ፥ መንግሥታትንም ለማከማቸት ነው፥ ይህም መዓቴንና የቁጣዬን ትኩሳት ሁሉ ለማፍሰስ ነው፤ በቅንዓቴ እሳት ምድርም ሁሉ ትበላለችና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል “ጥቂት ታገሡ፤ በእነርሱ ላይ የምፈርድበት ጊዜ ይመጣል፤ ሕዝቦችንና መንግሥታትን ሰብስቤ ኀይለኛ ቊጣዬን አወርድባቸዋለሁ፤ ከቊጣዬም ኀይለኛነት የተነሣ መላዋ ምድር ትጠፋለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መዓቴንና የቍጣዬን ትኵሳት ሁሉ አፈስስባቸው ዘንድ ፍርዴ አሕዛብን ለመሰብሰብ፥ መንግሥታትንም ለማከማቸት ነውና፥ ምድርም ሁሉ በቅንዓቴ እሳት ትበላለችና ስለዚህ ለመበዝበዝ እስከምነሣበት ቀን ድረስ ጠብቁኝ፥ ይላል እግዚአብሔር። |
አምላኬ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ፤ ነፍሴ አንተን ተጠማች፥ እንጨትና ውኃ በሌለበት ምድረ በዳ ሥጋዬን ለአንተ እንዴት ልዘርጋልህ
እንደ ቀለበት በልብህ፥ እንደ ቀለበትም ማኅተም በክንድህ አኑረኝ፤ ፍቅር እንደ ሞት የበረታች ናትና፥ ቅንዐትም እንደ ሲኦል የጨከነች ናትና። ላንቃዋ እንደ እሳት ላንቃ እንደ ነበልባል ነው።
አምላካችን እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና ስለዚህ እግዚአብሔር ይራራላችሁ ዘንድ ይታገሣል፤ ይምራችሁም ዘንድ ከፍ ከፍ ይላል፤ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ብፁዓን ናቸው።
የእግዚአብሔር ቍጣ በአሕዛብ ሁሉ ላይ ነውና፤ መቅሠፍቱም ያጠፋቸውና ለጦር ይሰጣቸው ዘንድ በቍጥራቸው ልክ ነው።
ያዕቆብን በልተውታልና፥ አጥፍተውትማልና፥ ማደሪያውንም አፍርሰዋልና በማያውቁህ አሕዛብ፥ ስምህንም በማይጠሩ ትውልድ ላይ መዓትህን አፍስስ።
አሕዛብን ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደ ኢዮሳፍጥም ሸለቆ አወርዳቸዋለሁ፤ በአሕዛብም መካከል በተበተኑበትና ምድሬን በተካፈሉበት በዚያ ስለ ወገኖች ስለ ርስቴ ስለ እስራኤል እወቅሳቸዋለሁ።
ራእዩ ገና እስከ ተወሰነው ጊዜ ነው፥ ወደ ፍጻሜውም ይቸኵላል፥ እርሱም አይዋሽም፣ ቢዘገይም በእርግጥ ይመጣልና ታገሠው፣ እርሱ አይዘገይም።
በእግዚአብሔርም ቍጣ ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፣ እርሱም በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ፈጥኖ ይጨርሳቸዋልና ምድር ሁሉ በቅንዓቱ እሳት ትበላለች።
የመንግሥታትንም ዙፋን እገለብጣለሁ፥ የአሕዛብንም መንግሥታት ኃይል አጠፋለሁ፣ ሰረገሎችንና የሚቀመጡባቸውንም እገለብጣለሁ፣ ፈረሶችና ፈረሰኞቻቸውም እያንዳንዳቸው በወንድማቸው ሰይፍ ይወድቃሉ።
የጌታው ቀን ግን እንደ ሌባ ሆኖ ይመጣል፤ በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፤ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይቀልጣል፤ ምድርም በእርስዋም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል።
ምልክት እያደረጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸውና፥ በታላቁም ሁሉን በሚገዛ በእግዚአብሔር ቀን ወደሚሆነው ጦር እንዲያስከትቱአቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገሥታት ይወጣሉ።