La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሶፎንያስ 2:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

መንጎችም የምድርም አራዊት ሁሉ በውስጥዋ ይመሰጋሉ፣ ይብራና ጃርት በዓምዶችዋ መካከል ያድራሉ፣ ድምፃቸው በመስኮቶችዋ ይጮኻል፣ የዝግባም እንጨት ሥራ ይገለጣልና በመድረኮችዋ ላይ ጥፋት ይሆናል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የበግና የከብት መንጋዎች፣ የፍጥረት ዐይነት ሁሉ በውስጧ ይመሰጋሉ፤ ጕጕትና ጃርት፣ በግንቦቿ ላይ ያድራሉ። ጩኸታቸው በየመስኮቱ ያስተጋባል፤ ፍርስራሽ በየደጃፉ ይከመራል፤ ከዝግባ የተሠሩ ተሸካሚዎችም ይገለጣሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

መንጎችም የምድርም አራዊት ሁሉ በውስጧ ይኖራሉ፥ ጉጉትና ጃርት በዓምዶችዋ መካከል ያድራሉ፥ ድምፅም በመስኮት ይጮኻል፥ በመድረኩ ላይ ጥፋት ይደርሳል የዝግባ እንጨት ሥራ ይገለጣልና።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የአራዊት መንጋዎች በእርስዋ ይኖራሉ፤ ልዩ ልዩ ዐይነት ጒጒቶች በጒልላትዋ ላይ ይኖራሉ፤ በየመስኮቱም ይጮኻሉ፤ በሊባኖስ ዛፍ የተሠራው ወለል ስለሚላቀቅ በመድረኩ ላይ ጥፋት ይደርሳል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

መንጎችም የምድርም አራዊት ሁሉ በውስጥዋ ይመሰጋሉ፥ ይብራና ጃርት በዓምዶችዋ መካከል ያድራሉ፥ ድምፃቸው በመስኮቶችዋ ይጮኻል፥ የዝግባም እንጨት ሥራ ይገለጣልና በመድረኮችዋ ላይ ጥፋት ይሆናል።

Ver Capítulo



ሶፎንያስ 2:14
8 Referencias Cruzadas  

እግ​ዝ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ርታ አድ​ራጊ ነው፤ ለተ​በ​ደሉ ሁሉ ይፈ​ር​ዳል።


“ባቢ​ሎ​ንን የወ​ፎች መኖ​ሪያ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ እንደ ኢም​ን​ትም ትሆ​ና​ለች፤ በጥ​ፋ​ትም እንደ ረግ​ረግ ጭቃ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ” ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“ለራሴ ሰፊ ቤት፥ ትል​ቅም ሰገ​ነት እሠ​ራ​ለሁ ለሚል፥ መስ​ኮ​ት​ንም ለሚ​ያ​ወጣ፥ በዝ​ግ​ባም ሥራ ለሚ​ያ​ስ​ጌጥ፥ በቀይ ቀለ​ምም ለሚ​ቀ​ባው ወዮ​ለት፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በመ​ሠ​ው​ያው ላይ ቆሞ አየ​ሁት፤ እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፥ “አበ​ቦች የተ​ሳ​ሉ​ባ​ቸ​ውን ምሰ​ሶ​ዎ​ችን ምታ፤ መድ​ረ​ኮ​ቹም ይና​ወ​ጣሉ፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም ቍረጥ፤ እኔም ከእ​ነ​ርሱ የቀ​ሩ​ትን በሰ​ይፍ እገ​ድ​ላ​ለሁ፤ ከሚ​ሸ​ሹ​ትም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም፤ ከሚ​ያ​መ​ል​ጡ​ትም የሚ​ድን የለም።


ቀርጤስም የእረኞች መኖሪያና የመንጎች በረት ይሆናል።


በብርቱም ድምፅ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፤ የርኵሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኵሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤