ኤልሳዕም በሚሞትበት በሽታ ታመመ፤ የእስራኤልም ንጉሥ ዮአስ ወደ እርሱ ወርዶ በፊቱ አለቀሰና፥ “አባቴ ሆይ፥ አባቴ ሆይ፥ የእስራኤል ሰረገላቸውና ፈረሰኛቸው” አለ።
ዘካርያስ 1:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቶቻችሁ ወዴት ናቸው? ነቢያትስ ለዘላለም በሕይወት ይኖራሉን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባቶቻችሁ አሁን የት አሉ? ነቢያትስ ለዘላለም በሕይወት ይኖራሉን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባቶቻችሁ ወዴት ናቸው? ነቢያትስ ለዘለዓለም በሕይወት መኖር የሚችሉ ይመስላችኋልን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቀድሞ አባቶቻችሁ አሁን የት አሉ? ነቢያቱስ ለዘለዓለም ይኖራሉን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባቶቻችሁ ወዴት ናቸው? ነቢያትስ ለዘላለም በሕይወት ይኖራሉን? |
ኤልሳዕም በሚሞትበት በሽታ ታመመ፤ የእስራኤልም ንጉሥ ዮአስ ወደ እርሱ ወርዶ በፊቱ አለቀሰና፥ “አባቴ ሆይ፥ አባቴ ሆይ፥ የእስራኤል ሰረገላቸውና ፈረሰኛቸው” አለ።
ከፍ ያለውን ተመልክተው ደግሞ ሲፈሩ፥ ድንጋጤም በመንገድ ላይ ሲሆን፤ ለውዝም ሲያብብ፥ አንበጣም እንደ ሸክም ሲከብድ፥ ፍሬም ሳይበተን፤ ሰው ወደ ዘለዓለም ቤቱ ሲሄድ፥ አልቃሾችም በአደባባይ ሲዞሩ፤
አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፥ ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ በሥጋም በነበረበት ጊዜ መልካም ወይም ክፉ ቢሆን ስለ ሠራው ሁሉ መልስ ሳይሰጥ ፈጣሪህን አስብ።
“ዳግመኛም ሌላ ክርታስ ውሰድ፤ የይሁዳም ንጉሥ ኢዮአቄም በአቃጠለው ክርታስ ላይ የነበረውን የቀድሞውን ቃል ሁሉ ጻፍበት።
አይሁድም እንዲህ አሉት፥ “አሁን ጋኔን እንዳለብህ ዐወቅን፤ አብርሃም ስንኳ ሞቶአል፤ ነቢያትም ሞተዋል፤ አንተ ግን ቃሌን የሚጠብቅ ለዘለዓለም ሞትን አይቀምስም ትላለህ።
ዳዊት ግን በዘመኑ ለእግዚአብሔር ትእዛዝ አገልግሎአል፤ እንደ አባቶቹ ሞተ፥ ተቀበረም፤ መፍረስ መበስበስንም አይቶአል።
ሳሙኤልም ሞተ፤ እስራኤልም ሁሉ ተሰብስበው አለቀሱለት፤ በአርማቴምም በቤቱ ቀበሩት። ዳዊትም ተነሥቶ ወደ ማዖን ምድረ በዳ ወረደ።