ብታምንበት ይቀድስሃል፤ እንደ ድንጋይ ዕንቅፋትም አያደናቅፍህም፤ እንደሚያድጥ ዓለትም አይሆንብህም፤ ሁለቱ የያዕቆብ ቤቶች ግን በኢየሩሳሌም በወጥመድና በአሽክላ ተይዘው ይኖራሉ።
ሮሜ 9:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህስ ስለምን ነው? ጽድቃቸው የኦሪትን ሥራ በመሥራት እንጂ በእምነት ስለ አልሆነ ነው፤ የእንቅፋት ድንጋይ አሰነካከላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ ለምን ሆነ? በእምነት ሳይሆን በሥራ እንደ ሆነ አድርገው በመቍጠር ስለ ተከታተሉት ነው፤ እነርሱም፣ “በማሰናከያው ድንጋይ” ተሰናከሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለምን? ምክንያቱም በእምነት ሳይሆን በሥራ እንደሆነ ስለቆጠሩት ነው፤ ስለዚህ በማሰናከያ ድንጋይ ተሰናከሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስለምን ወደ ጽድቅ አልደረሱም?” ቢባል እነርሱ ጽድቅን ለማግኘት የፈለጉት በእምነት ሳይሆን በሥራ ስለ ሆነ ነው፤ ስለዚህ በማሰናከያ ድንጋይ ተሰናከሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህስ ስለ ምንድር ነው? በሥራ እንጂ በእምነት ጽድቅን ስላልተከተሉ ነው፤ እነሆ፥ በጽዮን የእንቅፋት ድንጋይና የማሰናከያ ዓለት አኖራለሁ በእርሱም የሚያምን አያፍርም ተብሎ እንደ ተጻፈ በእንቅፋት ድንጋይ ተሰናከሉ። |
ብታምንበት ይቀድስሃል፤ እንደ ድንጋይ ዕንቅፋትም አያደናቅፍህም፤ እንደሚያድጥ ዓለትም አይሆንብህም፤ ሁለቱ የያዕቆብ ቤቶች ግን በኢየሩሳሌም በወጥመድና በአሽክላ ተይዘው ይኖራሉ።
ስምዖንም ባረካቸው፤ እናቱን ማርያምንም እንዲህ አላት፤ “እነሆ፥ ይህ ሕፃን ከእስራኤል መካከል ለብዙዎች ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው፥ ለሚቃወሙትም ምልክት ይሆን ዘንድ የተሠየመ ነው፤
የእግዚአብሔርን ጽድቅ አያውቁአትምና በራሳቸውም ጽድቅ ጸንተው ሊኖሩ ወደዱ፤ ለእግዚአብሔር ጽድቅ ግን መገዛት ተሳናቸው።
እንግዲህ እላለሁ፤ ሊወድቁ ተሰናከሉን? አይደለም፤ ነገር ግን እስራኤል ይቀኑ ዘንድ እነርሱ በመሰናከላቸው ለአሕዛብ ድኅነት ሆነ።
ስለዚህም እግዚአብሔር ለአብርሃምና ለዘሩ የሰጠው ተስፋ የታመነ ይሆን ዘንድ፥ የሚጸድቁ በእምነት እንጂ የኦሪትን ሥራ በመፈጸም ብቻ እንዳይደለ ያውቁ ዘንድ እግዚአብሔር ጽድቅን በእምነት አደረገ።