Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ማቴዎስ 13:57 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

57 ኢየሱስ ግን “ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ቤቱ በቀር ሳይከበር አይቀርም፤” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

57 ከዚህም የተነሣ ተሰናከሉበት። ኢየሱስ ግን፣ “ነቢይ የማይከበረው በራሱ አገርና በራሱ ቤት ብቻ ነው” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

57 ተሰናከሉበትም። ኢየሱስ ግን “ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ቤቱ በስተቀር ሳይከበር አይቀርም፤” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

57 በዚህም ምክንያት ተሰናክለውበት ሳይቀበሉት ቀሩ። ኢየሱስ ግን፦ “ነቢይ የማይከበረው በሀገሩና በገዛ ቤቱ ብቻ ነው” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

57 ኢየሱስ ግን፦ ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ቤቱ በቀር ሳይከበር አይቀርም አላቸው።

Ver Capítulo Copiar




ማቴዎስ 13:57
19 Referencias Cruzadas  

ነቢይ በገዛ ሀገሩ እን​ደ​ማ​ይ​ከ​ብር እርሱ ራሱ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ መሰ​ከረ።


ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል፤ በእኔም የማይሰናከለው ሁሉ ብፁዕ ነው።”


እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ነቢይ በሀ​ገሩ አይ​ከ​ብ​ርም።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ስለ​ዚህ ነገር እንደ አን​ጐ​ራ​ጐሩ በልቡ ዐወ​ቀ​ባ​ቸ​ውና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ይህ ያሰ​ና​ክ​ላ​ች​ኋ​ልን?


መል​ኩም የተ​ናቀ፥ ከሰ​ውም ልጆች ሁሉ የተ​ዋ​ረደ፥ የተ​ገ​ረፈ ሰው፥ መከ​ራ​ንም የተ​ቀ​በለ ነው፤ ፊቱ​ንም መል​ሶ​አ​ልና አቃ​ለ​ሉት፥ አላ​ከ​በ​ሩ​ት​ምም።


“እኛ አባ​ቱ​ንና እና​ቱን የም​ና​ው​ቃ​ቸው ይህ የዮ​ሴፍ ልጅ ኢየ​ሱስ አይ​ደ​ለ​ምን? እን​ግ​ዲህ እን​ዴት ከሰ​ማይ ወረ​ድሁ ይለ​ናል?” አሉ።


በእ​ኔም የማ​ይ​ሰ​ና​ከል ብፁዕ ነው።”


ታዳ​ጊህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሕይ​ወ​ቱን የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቃ​ትን፥ በአ​ሕ​ዛብ የተ​ጠ​ላ​ውን የአ​ለ​ቆ​ችን ባርያ ቀድ​ሱት፤ ነገ​ሥ​ታት ያዩ​ታል፤ አለ​ቆ​ችም ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብለው ተነ​ሥ​ተው ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ታማኝ ነውና፥ እኔም መር​ጨ​ሃ​ለ​ሁና።”


ብታ​ም​ን​በት ይቀ​ድ​ስ​ሃል፤ እንደ ድን​ጋይ ዕን​ቅ​ፋ​ትም አያ​ደ​ና​ቅ​ፍ​ህም፤ እን​ደ​ሚ​ያ​ድጥ ዓለ​ትም አይ​ሆ​ን​ብ​ህም፤ ሁለቱ የያ​ዕ​ቆብ ቤቶች ግን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በወ​ጥ​መ​ድና በአ​ሽ​ክላ ተይ​ዘው ይኖ​ራሉ።


ስሙም ተገልጦአልና ንጉሡ ሄሮድስ በሰማ ጊዜ “መጥምቁ ዮሐንስ ከሙታን ተነሥቶአል፤ ስለዚህም ኀይል በእርሱ ይደረጋል፤” አለ።


ይህስ ጸራቢው የማርያም ልጅ የያቆብም የዮሳም የይሁዳም የስምዖንም ወንድም አይደለምን? እኅቶቹስ በዚህ በእኛ ዘንድ አይደሉምን?” አሉ፤ ይሰናከሉበትም ነበር።


በአለማመናቸውም ምክንያት በዚያ ብዙ ተአምራት አላደረገም።


ከዚያም ወጥቶ ወደ ገዛ አገሩ መጣ፤ ደቀ መዛሙርቱም ተከተሉት።


ኢየሱስም “ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ዘመዶቹ ከገዛ ቤቱም በቀር ሳይከበር አይቀርም፤” አላቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios