በሄዱም ጊዜ ይሄዳሉ፤ በቆሙም ጊዜ ይቆማሉ፤ በእነዚያ መንኰራኵሮች ውስጥ የሕይወት መንፈስ አለና ከምድር በተነሡ ጊዜ መንኰራኵሮቹ ከእነርሱ ጋር ይነሣሉ።
ሮሜ 8:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኢየሱስ ክርስቶስ የተሰጠን ሕይወት የሚገኝበት የመንፈስ ሕግ እርሱ ከኀጢአትና ከሞት ሕግ ነጻ አውጥቶናልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም የሕይወት መንፈስ ሕግ በክርስቶስ ኢየሱስ ከኀጢአትና ከሞት ሕግ ነጻ አውጥቷችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ ነፃ አውጥቶኛልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በኢየሱስ ክርስቶስ የሚገኘውን ሕይወት የሚሰጥ የመንፈስ ቅዱስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ ነጻ አውጥቶኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ አርነት አውጥቶኛልና። |
በሄዱም ጊዜ ይሄዳሉ፤ በቆሙም ጊዜ ይቆማሉ፤ በእነዚያ መንኰራኵሮች ውስጥ የሕይወት መንፈስ አለና ከምድር በተነሡ ጊዜ መንኰራኵሮቹ ከእነርሱ ጋር ይነሣሉ።
ጌታችን ኢየሱስም፥ “የእግዚአብሔርን ስጦታና ውኃ አጠጪኝ ብሎ የሚለምንሽ ማን እንደ ሆነ ብታውቂስ አንቺ ደግሞ በለመንሺው ነበር፤ እርሱም የሕይወትን ውኃ በሰጠሽ ነበር” ብሎ መለሰላት።
እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ግን ለዘለዓለም አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውኃ በውስጡ ለዘለዓለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆንለታል እንጂ።”
ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ግን አንዳች አይጠቅምም፤ ይህም እኔ የምነግራችሁ ቃል መንፈስ ነው፤ ሕይወትም ነው።
ኀጢአትም ሞትን እንደ አነገሠችው እንዲሁ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ጸጋ ጽድቅን ለዘለዓለም ሕይወት ታነግሠዋለች።
ዛሬ ግን ከኀጢአት ነጻ ወጣችሁ፤ ራሳችሁንም ለጽድቅ አስገዛችሁ፤ ለቅድስናም ፍሬን አፈራችሁ፤ ፍጻሜው ግን የዘለዓለም ሕይወት ነው።
ነገር ግን በሰውነቴ ውስጥ ያለውን ሌላ የኀጢአት ሕግ እመለከታለሁ፤ በልቡናዬም ውስጥ ካለው ከእግዚአብሔር ሕግ ጋር ተሰልፈው ተዋጉ፤ በሰውነቴ ውስጥ ያለው ያ የኀጢአት ሕግም በረታና ወደ እርሱ ማረከኝ።
ወንድሞች ሆይ! እናንተ እንዲሁ የክርስቶስ አካል ስለ ሆናችሁ ከኦሪት ተለይታችኋል፤ ለእግዚአብሔርም ፍሬ እንድታፈሩ ከሙታን ተለይቶ ለተነሣው ለዳግማዊ አዳም ሆናችኋል።
መጽሐፍ እንዲሁ ብሎአልና የመጀመሪያው ሰው አዳም በነፍስ ሕያው ሆኖ ተፈጠረ፤ ሁለተኛው አዳም ግን ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው።
በመንፈስ እንጂ በፊደል ለማይሆን ለአዲስ ሕግ አገልጋዮች አደረገን፤ ፊደል ይገድላል፥ መንፈስ ግን ሕያው ያደርጋል።
ከሦስቱ ቀን ተኵልም በኋላ ከእግዚአብሔር የወጣ የሕይወት መንፈስ ገባባቸው፤ በእግሮቻቸውም ቆሙ፤ ታላቅም ፍርሃት በሚመለከቱት ላይ ወደቀባቸው።