ሮሜ 7:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም ቀድሞ ኦሪት ሳትሠራ ሕያው ነበርሁ፤ የኦሪት ትእዛዝ በመጣች ጊዜ ግን ኀጢአት ሕይወትን አገኘች፤ እኔ ግን ሞትሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕጉ ሳይኖር ሕያው ነበርሁ፤ ትእዛዝ ከመጣ በኋላ ግን፣ ኀጢአት ሕያው ሆነ፤ እኔም ሞትሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም ድሮ ያለ ሕግ ሕያው ነበርሁ፤ ትእዛዝ በመጣ ጊዜ ግን ኃጢአት ሕያው ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀድሞ ሕግ ባልነበረበት ጊዜ እኔ በሕይወት እኖር ነበር፤ የሕግ ትእዛዝ በመጣ ጊዜ ግን እኔ ሞቼ ኃጢአት ሕይወት አገኘ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም ዱሮ ያለ ሕግ ሕያው ነበርሁ፤ ትእዛዝ በመጣች ጊዜ ግን ኃጢአት ሕያው ሆነ እኔም ሞትሁ፤ |
መልሶም አባቱን እንዲህ አለው፦ ‘እነሆ፥ ይህን ያህል ዓመት ተገዛሁልህ፤ ፈጽሞ ከትእዛዝህ አልወጣሁም፤ ለእኔ ግን ከባልንጀሮች ጋር ደስ እንዲለኝ አንድ የፍየል ጠቦት እንኳ አልሰጠኸኝም።
ወንድሞች ሆይ! እናንተ እንዲሁ የክርስቶስ አካል ስለ ሆናችሁ ከኦሪት ተለይታችኋል፤ ለእግዚአብሔርም ፍሬ እንድታፈሩ ከሙታን ተለይቶ ለተነሣው ለዳግማዊ አዳም ሆናችኋል።
አሁን ግን ታስረንበት ከነበረው ከኦሪት ሕግ ነፃ ወጥተናል፤ ስለዚህ በብሉይ መጽሐፍ ሳይሆን በአዲሱ መንፈሳዊ ሕይወት እንገዛለን።
ያችም ትእዛዝ ለኀጢአት ምክንያት ሆነቻት፤ ምኞትንም ሁሉ አመጣችብኝ፤ ቀድሞ ግን ኦሪት ሳትሠራ ኀጢአት ሙት ነበረች።
በኦሪት ሕግ ያሉ ሁሉ በእርግማን ውስጥ ይኖራሉ፤ መጽሐፍ እንዲህ ብሎአልና፥ “በዚህ በኦሪት መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈውን ሁሉ የማይፈጽምና የማይጠብቅ ርጉም ይሁን።”