La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሮሜ 7:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

መል​ካም ሥራ እን​ድ​ሠራ የፈ​ቀ​ደ​ል​ኝን ያን ሕግ እርሱ ክፉ ነገር አም​ጥ​ቶ​ብኝ አገ​ኘ​ሁት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ ይህ ሕግ እየሠራ እንደ ሆነ ተረድቻለሁ፤ ይኸውም በጎ ነገር ለመሥራት ስፈልግ፣ ክፋት ከእኔ ጋራ አለ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህ መልካም ነገርን ማድረግ ስፈልግ ክፋት ወደ እኔ ይቀርባል፤ ይኸውም ሕግ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ ሕግ በሥራ ላይ ውሎ አያለሁ፤ መልካም ነገርን ማድረግ ስፈልግ ክፉ ነገርን ለማድረግ እገደዳለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንግዲያስ መልካሙን አደርግ ዘንድ ስወድ በእኔ ክፉ እንዲያድርብኝ ሕግን አገኛለሁ።

Ver Capítulo



ሮሜ 7:21
19 Referencias Cruzadas  

እኔን ግን ስለ የዋ​ህ​ነቴ ተቀ​በ​ል​ኸኝ፥ በፊ​ት​ህም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጸ​ና​ኸኝ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዲህ በሉት፥ “ሥራህ ግሩም ነው፤ ኀይ​ልህ ብዙ ሲሆን ጠላ​ቶ​ችህ ዋሹ​ብህ።”


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መን​ፈስ ቅዱ​ስን ተመ​ልቶ ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ተመ​ለሰ፤ መን​ፈ​ስም ወደ ምድረ በዳ ወሰ​ደው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ኀጢ​ኣ​ትን የሚ​ሠራ ሁሉ የኀ​ጢ​ኣት ባርያ ነው።


በዚህ በሚ​ሞት ሰው​ነ​ታ​ችሁ ኀጢ​አ​ትን አታ​ን​ግ​ሡ​አት፤ ለም​ኞ​ቱም እሽ አት​በ​ሉት።


እን​ግ​ዲህ ኀጢ​አት አት​ገ​ዛ​ች​ሁም፤ የኦ​ሪ​ትን ሕግ ከመ​ሥ​ራት ወጥ​ታ​ችሁ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ገብ​ታ​ች​ኋ​ልና።


ነገር ግን በሰ​ው​ነቴ ውስጥ ያለ​ውን ሌላ የኀ​ጢ​አት ሕግ እመ​ለ​ከ​ታ​ለሁ፤ በል​ቡ​ና​ዬም ውስጥ ካለው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ጋር ተሰ​ል​ፈው ተዋጉ፤ በሰ​ው​ነቴ ውስጥ ያለው ያ የኀ​ጢ​አት ሕግም በረ​ታና ወደ እርሱ ማረ​ከኝ።


በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤ እኔ በልቤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ እገ​ዛ​ለሁ፤ በሥ​ጋዬ ግን ለኀ​ጢ​አት ሕግ እገ​ዛ​ለሁ።


በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የተ​ሰ​ጠን ሕይ​ወት የሚ​ገ​ኝ​በት የመ​ን​ፈስ ሕግ እርሱ ከኀ​ጢ​አ​ትና ከሞት ሕግ ነጻ አው​ጥ​ቶ​ና​ልና።


ስለ​ዚ​ህም የሕ​ዝ​ብን ኀጢ​አት ለማ​ስ​ተ​ስ​ረይ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሆ​ነው ነገር ሁሉ የሚ​ም​ርና የታ​መነ ሊቀ ካህ​ናት እን​ዲ​ሆን በነ​ገር ሁሉ ወን​ድ​ሞ​ቹን ሊመ​ስል ተገ​ባው።


ሊቀ ካህ​ና​ታ​ችን ለድ​ካ​ማ​ችን መከራ መቀ​በ​ልን የማ​ይ​ችል አይ​ደ​ለ​ምና፤ ነገር ግን ከብ​ቻዋ ከኀ​ጢ​አት በቀር እኛን በመ​ሰ​ለ​በት ሁሉ የተ​ፈ​ተነ ነው።


ራሳቸው የጥፋት ባሪያዎች ሆነው “አርነት ትወጣላችሁ፤” እያሉ ተስፋ ይሰጡአቸዋል፤ ሰው ለተሸነፈበት ለእርሱ ተገዝቶ ባሪያ ነውና።