Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሮሜ 7:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤ እኔ በልቤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ እገ​ዛ​ለሁ፤ በሥ​ጋዬ ግን ለኀ​ጢ​አት ሕግ እገ​ዛ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ምስጋና ለእግዚአብሔር ይሁን! እንግዲያስ እኔ ራሴ በአእምሮዬ ለእግዚአብሔር ሕግ ባሪያ ስሆን፣ በኀጢአተኛ ተፈጥሮዬ ግን ለኀጢአት ሕግ ባሪያ ነኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። እንግዲያስ እኔ ራሴ በአእምሮዬ ለእግዚአብሔር ሕግ ባርያ ስሆን፥ በሥጋዬ ግን ለኃጢአት ሕግ ባርያ ነኝ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለሚያድነኝ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን! እንግዲህ እኔ በአእምሮዬ፥ ለእግዚአብሔር ሕግ ተገዢ ስሆን በሥጋ ባሕርዬ ለኃጢአት ሕግ ተገዢ ሆኜአለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 በኢየሱስ ክርስቶስ በጌታችን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። እንግዲያስ እኔ በአእምሮዬ ለእግዚአብሔር ሕግ፥ በሥጋዬ ግን ለኃጢአት ሕግ እገዛለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 7:25
20 Referencias Cruzadas  

በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ትላ​ለህ፥ “አቤቱ፥ ተቈ​ጥ​ተ​ኸ​ኛ​ልና፥ ቍጣ​ህ​ንም ከእኔ መል​ሰ​ሃ​ልና፥ ዳግ​መ​ኛም ይቅር ብለ​ኸ​ኛ​ልና አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን ይቅር ብሎ​አ​ልና፥ ከሕ​ዝ​ቡም ችግ​ረ​ኞ​ቹን አጽ​ን​ቶ​አ​ልና። ሰማ​ያት ሆይ፥ ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ምድ​ርም ደስ ይበ​ላት፤ ተራ​ሮ​ችም እልል ይበሉ።


የተ​ጋ​ዙ​ት​ንም፦ ውጡ፤ በጨ​ለ​ማም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን፦ ተገ​ለጡ፤ ትል ዘንድ።” በመ​ን​ገ​ድም ሁሉ ላይ ይሰ​ማ​ራሉ፤ ማሰ​ማ​ሪ​ያ​ቸ​ውም በጥ​ር​ጊያ ጎዳና ሁሉ ላይ ይሆ​ናል።


ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኀጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።”


እን​ግ​ዲህ ኀጢ​አት አት​ገ​ዛ​ች​ሁም፤ የኦ​ሪ​ትን ሕግ ከመ​ሥ​ራት ወጥ​ታ​ችሁ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ገብ​ታ​ች​ኋ​ልና።


የኀ​ጢ​አት ተገ​ዦች ስት​ሆኑ ምሳ​ሌ​ነቱ ለተ​ሰ​ጣ​ችሁ ለም​ት​ማ​ሩት ትም​ህ​ርት ታዝ​ዛ​ች​ኋ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።


በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የተ​ሰ​ጠን ሕይ​ወት የሚ​ገ​ኝ​በት የመ​ን​ፈስ ሕግ እርሱ ከኀ​ጢ​አ​ትና ከሞት ሕግ ነጻ አው​ጥ​ቶ​ና​ልና።


በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ድል መን​ሣ​ትን ለሰ​ጠን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ይሁን።


ስለ​ማ​ት​መ​ረ​መ​ርና ባላ​ሰ​ቡ​አት ጊዜ ስለ​ም​ት​መ​ጣው ጸጋው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።


ዘወ​ት​ርም ስለ ሁሉ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ ምስ​ጋና አቅ​ርቡ።


ግዙ​ራ​ንስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በመ​ን​ፈስ የም​ና​ገ​ለ​ግ​ለ​ውና የም​ና​መ​ል​ከው እኛ ነን፤ እኛም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እን​መ​ካ​ለን እንጂ በሥ​ጋ​ችን የም​ን​መካ አይ​ደ​ለም።


በም​ንም አት​ጨ​ነቁ፤ ነገር ግን በሁሉ ነገር ጸልዩ ማል​ዱም፤ እያ​መ​ሰ​ገ​ና​ች​ሁም ልመ​ና​ች​ሁን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግለጡ።


በቃ​ልም ቢሆን፥ ወይም በሥራ የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ትን ሁሉ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም አድ​ርጉ፤ ስለ እር​ሱም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብን አመ​ስ​ግ​ኑት።


እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።


እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos