ሮሜ 2:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕግ የሌላቸው አሕዛብስ እንኳ ለራሳቸው ሕግ ይሠራሉ፤ ራሳቸው ለራሳቸው ሕግን ይደነግጋሉ፤ በሕጋቸው የታዘዘውንም ያደርጋሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕግ የሌላቸው አሕዛብ ሕግ የሚያዝዘውን ነገር በተፈጥሮ ሲያደርጉ፣ ሕግ ባይኖራቸውም እነርሱ ለራሳቸው ሕግ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕግ የሌላቸው አሕዛብ፥ ሕግ የሚያዘውን ነገር በተፈጥሮአቸው ሲያደርጉ፥ እነዚያ ሕግ ባይኖራቸውም ለራሳቸው ሕግ ናቸውና፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕግ የሌላቸው አሕዛብ በተፈጥሮአቸው ሕግ የሚያዘውን ነገር ይፈጽማሉ፤ በዚህም ምክንያት ሕግ ባይኖራቸውም የራሳቸው የተፈጥሮ ሕግ ስላላቸው ማድረግ የሚገባቸውን ያውቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕግ የሌላቸው አሕዛብ ከባሕርያቸው የሕግን ትእዛዝ ሲያደርጉ፥ እነዚያ ሕግ ባይኖራቸው እንኳ ለራሳቸው ሕግ ናቸውና፤ |
የቀድሞውንስ ያለ ማወቅ ዘመን እግዚአብሔር አሳልፎታል፤ ዛሬ ግን በመላው ዓለም ንስሓ እንዲገቡ ሰውን ሁሉ አዝዞአል።
ይህን እንዲህ ላደረገ ሞት እንደሚገባው እነርሱ ራሳቸው የእግዚአብሔርን ፍርድ እያወቁ፥ እነርሱ ብቻ የሚያደርጉት አይደለም፤ ነገር ግን ሌላውን ያነሣሡታል፤ ያሠሩታልም።
በልባቸው የተጻፈውን የሕግ ሥራ ያሳያሉ፤ ከሥራቸውም የተነሣ ይታወቃል፤ ሕሊናቸውም ይመሰክርባቸዋል፤ ይፈርድባቸዋልም።
ተገዝረህ ኦሪትን ከምታፈርስ በተፈጥሮ ያገኘሃት አለመገዘርህ አብራህ ብትኖር ይሻልሃል፤ ኦሪትን ከምታፈርስ ከአንተ ከተገዘርኸው ያ ያልተገዘረው፥ ኦሪትን የሚፈጽመው ይሻላል።
የእግዚአብሔርን ሕግ የዘነጋሁ ሳልሆን፥ በክርስቶስ ሕግም ሳለሁ ሕግ የሌላቸውን እጠቅማቸው ዘንድ ሕግ ለሌላቸው ሕግ እንደሌለው ሆንሁላቸው።
ያንጊዜ ክርስቶስን አታውቁትም ነበር፤ ከእስራኤል ሕግ የተለያችሁ ነበራችሁ፤ ከተስፋው ሥርዐትም እንግዶች ነበራችሁ፤ ተስፋም አልነበራችሁም፤ በዚህም ዓለም እግዚአብሔርን አታውቁትም ነበር።
እኛ ሁላችን ቀድሞ እንደ ሥጋችን ምኞት ኖርን፤ የሥጋችንንም ፈቃድና ያሰብነውን አደረግን፤ እንደ ሌሎች ኃጥአንም ሁሉ የጥፋት ልጆች ሆንን።
አምላካችን እግዚአብሔር በምንጠራው ጊዜ ሁሉ እንደሚቀርበን፥ አምላኩ ወደ እርሱ የቀረበው ታላቅ ሕዝብ ማን ነው?
አሁንም ወንድሞቻችን ሆይ፥ እውነትን ሁሉ፥ ቅንነትንም ሁሉ፥ ጽድቅንም ሁሉ፥ ንጽሕናንም ሁሉ፥ ፍቅርንና ስምምነትንም ሁሉ፥ በጎነትም ቢሆን፥ ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን ሁሉ አስቡ።