እርሱም በምኵራብ በግልጥ ይናገር ጀመር፤ ጵርስቅላና አቂላም በሰሙት ጊዜ ወደ ማደሪያቸው ወስደው ፍጹም የእግዚአብሔርን መንገድ አስረዱት።
ሮሜ 16:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ከእኔ ጋር የተባበሩትን ጵርስቅላንና አቂላን ሰላም በሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በክርስቶስ ኢየሱስ ዐብረውኝ ለሚያገለግሉት ለጵርስቅላና ለአቂላ ሰላምታ አቅርቡልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በክርስቶስ ኢየሱስ አብረውኝ ለሚሠሩ ለፕሪስካና ለአኪላ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ተባባሪዎቼ ለሆኑት ለጵርስቅላና ለአቂላ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በክርስቶስ ኢየሱስ አብረውኝ ለሚሠሩ ለጵርስቅላና ለአቂላ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ |
እርሱም በምኵራብ በግልጥ ይናገር ጀመር፤ ጵርስቅላና አቂላም በሰሙት ጊዜ ወደ ማደሪያቸው ወስደው ፍጹም የእግዚአብሔርን መንገድ አስረዱት።
ስለ እኔ ሰውነታቸውን ለመከራ አሳልፈው ሰጥተዋልና፤ የማመሰግናቸውም እኔ ብቻ አይደለሁም፤ ከአሕዛብ ያመኑ ምእመናን ሁሉ ያመሰግኑአቸዋል እንጂ።
ከዘመዶች ወገን የሚሆኑትን ከእኔ ጋር ያመኑ እንድራናቆስንና ዩልያንን ሰላም በሉ፤ ቀደም ሲል ክርስቶስን እንደ አገለገሉ ሐዋርያት ያውቁአቸዋል።
ጌታችን ኢየሱስን ከሙታን ለይቶ ያስነሣው የእግዚአብሔር መንፈስ ካደረባችሁ ኢየሱስ ክርስቶስን ከሙታን ለይቶ ያስነሣው እርሱ አድሮባችሁ ባለ መንፈሱ ለሟች ሰውነታችሁ ሕይወትን ይሰጣታል።
በኢየሱስ ክርስቶስ የተሰጠን ሕይወት የሚገኝበት የመንፈስ ሕግ እርሱ ከኀጢአትና ከሞት ሕግ ነጻ አውጥቶናልና።
በእስያ ያሉ ምእመናን ሰላምታ ያቀርቡላችኋል፤ አቂላና ጵርስቅላ በቤታቸው ከእነርሱ ጋር ያሉ ምእመናንም ሁሉ በጌታችን እጅግ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
በክርስቶስ ያመነ አንድ ሰው አውቃለሁ፤ ዘመኑ ከዐሥራ አራት ዓመት በፊት ነው፤ ነገር ግን በሥጋው ይሁን በነፍሱ እንጃ፥ እግዚአብሔር ያውቃል፤ ያን ሰው እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ ነጥቀው ወሰዱት።
አሁንም አብሮኝ የሚሠራውን ወንድማችንን አፍሮዲጡን ወደ እናንተ ልልከው አስቤአለሁ፤ እርሱም የክርስቶስ ሎሌ ነው፤ ለእናንተም መምህራችሁ ነው፤ ለእኔም ለችግሬ ጊዜ መልእክተኛዬ ነው።
ኢዮስጦስ የተባለ ኢያሱም፥ ከግዙራን ሰዎች ወገን የሚሆኑ እነዚህ ሰላም ይሏችኋል። በእግዚአብሔር መንግሥት ሥራ ረዳቶች እነዚህ ብቻ ናቸው፤ እነርሱም እኔን አጽናንተውኛል።