ደግሞም አንድ ልብ ይሰጣቸው ዘንድ፥ በእግዚአብሔርም ቃል የሆነውን የንጉሡንና የአለቆቹን ትእዛዝ ያደርጉ ዘንድ የእግዚአብሔር እጅ በእነርሱ ላይ ሆነ።
ሮሜ 15:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የትዕግሥትና የመጽናናት አምላክ እግዚአብሔር እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ፈቃድ እርስ በርሳችን አንድ ዐሳብ መሆንን ይስጠን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብርታትንና መጽናናትን የሚሰጥ አምላክ፣ ክርስቶስ ኢየሱስን ስትከተሉ፣ በመካከላችሁ አንድ ሐሳብ ይስጣችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የትዕግሥትና የመጽናናት አምላክ እንደ ክርስቶስ ኢየሱስ እርስ በርሳችሁ በአንድ ሐሳብ መሆንን ይስጣችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የትዕግሥትና የመጽናናት አምላክ እርስ በርሳችሁ የኢየሱስ ክርስቶስን ምሳሌ በመከተል አብሮ የመኖርን ኅብረት ይስጣችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአንድ ልብ ሆናችሁ በአንድ አፍ እግዚአብሔርን፥ እርሱም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት፥ ታከብሩ ዘንድ፥ የትዕግሥትና የመጽናናት አምላክ እንደ ክርስቶስ ኢየሱስ ፈቃድ እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ መሆንን ይስጣችሁ። |
ደግሞም አንድ ልብ ይሰጣቸው ዘንድ፥ በእግዚአብሔርም ቃል የሆነውን የንጉሡንና የአለቆቹን ትእዛዝ ያደርጉ ዘንድ የእግዚአብሔር እጅ በእነርሱ ላይ ሆነ።
ለእነርሱም፥ ከእነርሱም በኋላ ለልጆቻቸው መልካም ይሆንላቸው ዘንድ ለዘለዓለም እንዲፈሩኝ ሌላ መንገድና ሌላ ልብ እሰጣቸዋለሁ።
ሌላ ልብ እሰጣቸዋለሁ፤ በውስጣቸውም አዲስ መንፈስ አሳድራለሁ፤ ከሥጋቸውም ውስጥ የድንጋዩን ልብ አወጣለሁ፤ የሥጋንም ልብ እሰጣቸዋለሁ፤
ያመኑትም ሁሉ አንድ ልብና አንዲት ነፍስ ሆነው ይኖሩ ነበር፤ በውስጣቸውም የሁሉ ገንዘብ በአንድነት ነበር እንጂ “ይህ የእኔ ገንዘብ ነው” የሚል አልነበረም።
እርስ በርሳችሁም በአንድ ዐሳብ ተስማሙ፤ ትዕቢትን ግን አታስቡ፤ ራሱን የሚያዋርደውንም ሰው ምሰሉ፤ እና ዐዋቆች ነን አትበሉ።
የተስፋ አምላክ እግዚአብሔርም በመንፈስ ቅዱስ ኀይል በተስፋ ያበዛችሁ ዘንድ በእምነት ደስታንና ሰላምን ሁሉ ይፈጽምላችሁ።
ወንድሞቻችን! አንድ ቃል እንድትናገሩ፥ እንዳታዝኑ፥ ፍጹማንም እንድትሆኑ፥ ሁላችሁንም፦ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እማልዳችኋለሁ፤ እንዳትለያዩም አንድ ልብና አንድ አሳብ ሆናችሁ ኑሩ።
ወድሞቻችን ሆይ፥ እንግዲህ ደስ ይበላችሁ፤ ጽኑ፤ ታገሡ፤ በአንድ ልብም ሁኑ፤ በሰላም ኑሩ፤ የሰላምና የፍቅር አምላክም ከእናንተ ጋር ይሁን።
ክርስቶስ እንደ ወደዳችሁ፥ ራሱንም ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ የሚሆን መሥዋዕትና ቍርባን አድርጎ እንደ ሰጠላችሁ በፍቅር ተመላለሱ።
ነገር ግን ምናልባት የመጣሁ እንደ ሆነ፥ ሳልኖርም ቢሆን በወንጌል ሃይማኖት እየተጋደላችሁ በአንድ መንፈስና በአንድ አካል ጸንታችሁ እንደምትኖሩ አይና እሰማ ዘንድ ሥራችሁ ለክርስቶስ ትምህርት እንደሚገባ ይሁን።
ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፤ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሓ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።