ሮሜ 12:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን፤ ከክፉ ራቁ፤ በጎውንም ያዙ፤ ለጽድቅ አድሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን፤ ክፉ የሆነውን ሁሉ ተጸየፉ፤ በጎ ከሆነው ነገር ጋራ ተቈራኙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍቅር እውነተኛ ይሁን፤ ክፉውን ነገር ተጸየፉ፥ መልካም የሆነው ነገር አጥብቃችሁ ያዙ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ግብዝነት የሌለበት እውነተኛ ፍቅር ይኑራችሁ፤ ክፉውን ነገር ጥሉ፤ መልካሙን ነገር ተከተሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን። ክፉውን ነገር ተጸየፉት፤ ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ፤ |
ሕዝብ እንደሚመጣ ወደ አንተ ይመጣሉ፤ እንደ ሕዝቤም በፊትህ ይቀመጣሉ፤ ቃልህንም ይሰማሉ፤ ነገር ግን አያደርጉትም፤ በአፋቸው ሐሰት ነገር አለና፥ ልባቸውም ጣዖታትን ይከተላልና።
ክፉውን ጥሉ፤ መልካሙንም ውደዱ፤ በበሩም አደባባይ ፍርድን አጽኑ፤ ምናልባት ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር ለዮሴፍ ቅሬታ ይራራ ይሆናል።
ይህንም ያለ፥ ድሆች አሳዝነውት አይደለም፤ ሌባ ነበርና፥ ሙዳየ ምጽዋቱንም ሲጠብቅ በውስጡ ከሚገባው ይወስድ ነበርና ስለዚህ ነው እንጂ።
በደረሰ ጊዜም የእግዚአብሔርን ጸጋ አየና ደስ አለው፤ በፍጹም ልባቸውም በእግዚአብሔር ጸንተው ይኖሩ ዘንድ መከራቸው።
በግድ የምላችሁ አይደለም፤ ነገር ግን ከእናንተ ለዚህ ሥራ የሚተጉለት አሉና የፍቅራችሁን እውነተኛነት አሁን መርምሬ ተረዳሁ።
“ጽድቅን ወደድህ፤ ዐመፃንም ጠላህ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር አምላክህ እንዳንተ ካሉት ይልቅ የሚበልጥ የደስታ ዘይትን ቀባህ።”
ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፤ በኋላም ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ፥ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት።