ሮሜ 10:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መጽሐፍ እንዲሁ፥ “ቃል ለልብህም ለአፍህም ቀርቦልሃል ይል የለምን?” ይህም የምንሰብከው የእምነት ቃል ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ምን ይላል? “ቃሉ በአጠገብህ ነው፤ በአፍህና በልብህም ውስጥ ነው፤” የምንሰብከውም የእምነት ቃል ይህ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ምን ይላል? ቃሉ በአጠገብህ ነው፤ በአፍህና በልብህም ነው፤ የምንሰብከው የእምነት ቃል ይህ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞም እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል፦ “የእግዚአብሔር ቃል አጠገብህ ነው፤ እንዲያውም በአፍህና በልብህ ነው፤” ይህም ቃል እኛ የምናበሥረው የእምነት ቃል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ምን ይላል? በአፍህ በልብህም ሆኖ ቃሉ ቀርቦልሃል፤ ይህም የምንሰብከው የእምነት ቃል ነው። |
በእናንተ ዘንድ ይህን ብቻ ላውቅ እወድዳለሁ፤ መንፈስ ቅዱስን የተቀበላችሁ የኦሪትን ሥራ በመሥራት ነውን? ወይስ ሃይማኖትን በመስማት?
እርሱ መንፈስ ቅዱስን የሚሰጣችሁ፥ ኀይልንም የሚያደርግላችሁ የኦሪትን ሥራ በመሥራት ነውን? ወይስ ሃይማኖትን በመስማት ነው?