Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሮሜ 10:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ኢየ​ሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአ​ፍህ ብት​መ​ሰ​ክር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሙ​ታን ለይቶ እንደ አስ​ነ​ሣው በል​ብህ ብታ​ምን ትድ​ና​ለህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “ኢየሱስ ጌታ ነው” ብለህ በአፍህ ብትመሰክር፣ እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን፣ ትድናለህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ምክንያቱም ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመሰክር፥ እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ኢየሱስ ጌታ መሆኑን በአፍህ ብትመሰክርና እግዚአብሔር ከሞት እንዳስነሣውም በልብህ ብታምን ትድናለህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 10:9
22 Referencias Cruzadas  

“እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ በሰው ፊት የሚ​ያ​ም​ን​ብ​ኝን ሁሉ እኔም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት ፊት አም​ነ​ዋ​ለሁ።


እነ​ር​ሱም፥ “በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እመን፤ አን​ተና ቤተ ሰብ​ህም ሁሉ ትድ​ና​ላ​ችሁ” አሉት።


አን​ደ​በ​ትም ሁሉ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ ክብር ጌታ እንደ ሆነ ያምን ዘንድ ነው።


የሚ​ፈ​ር​ድስ ማነው? የሞ​ተው፥ ይል​ቁ​ንም ከሙ​ታን ተለ​ይቶ የተ​ነ​ሣው፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቀኝ የተ​ቀ​መ​ጠው፥ ደግሞ ስለ እና የሚ​ፈ​ር​ደው ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “እኔ ሕያው ነኝ፤ ጕል​በ​ትም ሁሉ ለእኔ ይሰ​ግ​ዳል፤ አን​ደ​በ​ትም ሁሉ ለእኔ ይገ​ዛል።”


ስለ​ዚ​ህም ማንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ሲና​ገር፥ “ኢየ​ሱስ ውጉዝ ነው” የሚል እን​ደ​ሌለ፥ በመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም ካል​ሆነ በቀር “ኢየ​ሱስ ጌታ ነው” ሊል አን​ድስ እን​ኳን እን​ዳ​ይ​ችል አስ​ታ​ው​ቃ​ች​ኋ​ለሁ።


ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም ገብተዋልና፤ እነርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የማያምኑ ናቸው፤ ይህ አሳቹና የክርስቶስ ተቃዋሚው ነው።


ወላ​ጆቹ አይ​ሁ​ድን ስለ ፈሩ ይህን አሉ፥ “እርሱ ክር​ስ​ቶስ ነው ብሎ በእ​ርሱ የሚ​ያ​ምን ቢኖር ከም​ኵ​ራብ ይውጣ” ብለው አይ​ሁድ ተስ​ማ​ም​ተው ነበ​ርና።


በመ​ን​ገድ ሲሄ​ዱም ወደ ውኃ ደረሱ፤ ጃን​ደ​ረ​ባ​ውም፥ “እነሆ፥ ውኃ፥ መጠ​መ​ቅን ምን ይከ​ለ​ክ​ለ​ኛል?” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን የሞ​ትን ማሰ​ሪያ ፈቶ ከሙ​ታን ለይቶ አስ​ነ​ሣው፤ ሞት እር​ሱን ሊይ​ዘው አይ​ች​ል​ምና።


እር​ሱን ኢየ​ሱ​ስን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ነ​ሣው፤ ለዚ​ህም እኛ ሁላ​ችን ምስ​ክ​ሮቹ ነን።


ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን የተ​ሰ​ቀ​ለ​ውን፥ ሊያ​ስ​ነ​ሣ​ንና ሊያ​ጸ​ድ​ቀን የተ​ነ​ሣ​ውን ጌታ​ች​ንን ኢየ​ሱ​ስን ከሙ​ታን ለይቶ በአ​ስ​ነ​ሣው ስለ​ም​ና​ምን ስለ እናም ነው እንጂ።


በልቡ የሚ​ያ​ምን ይጸ​ድ​ቃ​ልና፤ በአ​ፉም የሚ​መ​ሰ​ክር ይድ​ና​ልና።


ስለ​ዚህ ሕያ​ዋ​ን​ንና ሙታ​ንን ይገዛ ዘንድ ክር​ስ​ቶስ ሞተ፥ ተነ​ሣም።


ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በሚታመን ሁሉ እግዚአብሔር በእርሱ ይኖራል እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios