ንጉሡም ዳዊት በጉባኤው መካከል ቆሞ እንዲህ አለ፥ “ወንድሞቼና ሕዝቤ ሆይ፥ ስሙኝ፤ ለእግዚአብሔር ለቃል ኪዳኑ ታቦትና ለአምላካችን እግር ማረፊያ የዕረፍት ቤት ለመሥራት አሳብ በልቤ መጣብኝ፤ ለዚህም ሥራ የሚያስፈልገውን አዘጋጅቻለሁ፤
መዝሙር 99:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ቸር፥ ምሕረቱም ለዘለዓለም፥ እውነቱም ለልጅ ልጅ ነውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላካችንን እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ አድርጉት፤ በእግሩ መርገጫ ስገዱ፤ እርሱ ቅዱስ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ አምላካችንን ከፍ ከፍ አድርጉት፥ ቅዱስ ነውና ወደ እግሩ መርገጫ ስገዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላካችን እግዚአብሔርን አመስግኑት! በእግሩ ማረፊያ ሥር ስገዱ! እርሱ ቅዱስ ነው። |
ንጉሡም ዳዊት በጉባኤው መካከል ቆሞ እንዲህ አለ፥ “ወንድሞቼና ሕዝቤ ሆይ፥ ስሙኝ፤ ለእግዚአብሔር ለቃል ኪዳኑ ታቦትና ለአምላካችን እግር ማረፊያ የዕረፍት ቤት ለመሥራት አሳብ በልቤ መጣብኝ፤ ለዚህም ሥራ የሚያስፈልገውን አዘጋጅቻለሁ፤
እግዚአብሔር እርሱ አምላካችን እንደ ሆነ ዕወቁ፤ እርሱ ፈጠረን፥ እኛም አይደለንም፤ እኛስ ሕዝቡ የመሰማርያውም በጎች ነን።
እኔን ለማዳን ረዳትና ሰዋሪ ሆነኝ፤ ይህ አምላኬ ነው፤ አመሰግነውማለሁ፤ የአባቴ አምላክ ነው፤ ከፍ ከፍም አደርገዋለሁ።
በዚያም ቀን እንዲህ ትላላችሁ፥ “እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ፤ በአሕዛብ መካከል ክብሩን አስታውቁ፤ ስሙ ከፍ ያለ እንደ ሆነ አስታውሱ።
እግዚአብሔር አምላኬ፥ ድንቅ ነገርን የዱሮ እውነተኛ ምክርን አድርገሃልና አከብርሃለሁ፤ ስምህንም አመሰግናለሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድን ነው?