አቤቱ ይህ ለአንተ አግባብ አይደለም፤ ይህን ነገር አታድርግ፤ ጻድቃንን ከኃጥኣን ጋር አታጥፋ፤ ምድርን ሁሉ የምትገዛ ይህን ፍርድ ታደርግ ዘንድ ለአንተ አግባብ አይደለም።”
መዝሙር 9:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ዓለምን በጽድቅ ይዳኛታል። አሕዛብንም በቅንነት ይዳኛቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዓለምን በጽድቅ ይዳኛል፤ ሕዝቦችንም በፍትሕ ይገዛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ግን ለዘለዓለም ይኖራል፥ ዙፋኑንም ለመፍረድ አዘጋጀ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዓለምን በፍትሕ ያስተዳድራል፤ ሕዝቦችንም በትክክል ይዳኛል። |
አቤቱ ይህ ለአንተ አግባብ አይደለም፤ ይህን ነገር አታድርግ፤ ጻድቃንን ከኃጥኣን ጋር አታጥፋ፤ ምድርን ሁሉ የምትገዛ ይህን ፍርድ ታደርግ ዘንድ ለአንተ አግባብ አይደለም።”
አምላካችን እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፥ በተቀደሰው ተራራ ይሰግዱለታል፤ አምላካችን እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና።
እግዚአብሔር ግን እውነተኛ አምላክ ነው፤ እርሱም ሕያው አምላክና የዘለዓለም ንጉሥ ነው፤ ከቍጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች፤ አሕዛብም መዓቱን አይችሉም።
በመረጠው ሰው እጅ በዓለም በእውነት የሚፈርድባትን ቀን ወስኖአልና፤ እርሱን ከሙታን ለይቶ በማስነሣቱም ብዙዎችን ወደ ሃይማኖት መልሶአልና።”
ይህም እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እኔ በወንጌል እንዳስተማርሁ ሰዎችን በልቡናቸው የሰወሩትንና የሸሸጉትን በሚመረምርበት ጊዜ የሚናገሩትና የሚመልሱት እንደሌለ ስለሚያውቁ ነው።