ድሃ ለዘለዓለም የሚረሳ አይደለምና፥ ችግረኞችም ተስፋቸውን ለዘለዓለም አያጡም።
ድኾችን ግን መቼም ቢሆን አይረሱም፤ የችግረኞችንም ተስፋ ለዘላለም መና ሆኖ አይቀርም።
ክፉዎች ወደ ሲኦል ይመለሳሉ፥ እግዚአብሔርን የሚረሱ አሕዛብም በሙሉ።
ችግረኞች ዘወትር እንደ ተረሱ አይቀሩም፤ የድኾችም ተስፋ ከንቱ ሆኖ ለዘለዓለም አይጠፋም።
የእግዚአብሔር ይቅርታው ግን ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም በሚፈሩት ላይ፥ ጽድቁም በልጅ ልጆች ላይ ነው፤
ቃሉን የምትፈጽሙ፥ ብርቱዎችና ኀያላን፥ የቃሉንም ድምፅ የምትሰሙ መላእክቱ ሁሉ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑት፤
እኔ ግን በቸርነትህ ታመንሁ፥ ልቤም በማዳንህ ደስ ይለዋል።
ፀሐይ በሚኖርበት ዘመን ሁሉ፥ በጨረቃም ፊት ለልጅ ልጅ ይኑር።
ለሞታቸው እረፍት የለውምና፤ ለመቅሠፍታቸውም ኀይል የለውምና፤
ደማቸውን የሚመራመር እርሱ አስቦአልና፥ የድሆችንም ጩኸት አልረሳምና።
ብትጠብቃቸው ዘመድ ይሆኑሃል፥ ተስፋህም አትጠፋም።
እንዲሁም ጥበብን በሰውነትህ ተማር፥ ብታገኛት ፍጻሜህ መልካም ይሆናል፥ ተስፋህም አይጠፋም።
የተራቡትን ከበረከቱ አጠገባቸው፤ ባለጠጎችንም ባዶ እጃቸውን ሰደዳቸው።
እርሱም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዐይኖቹን አንሥቶ እንዲህ አላቸው፥ “እናንተ ድሆች፥ ብፁዓን ናችሁ፤ የእግዚአብሔር መንግሥት የእናንተ ናትና።
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ባለ ጠጎች እንዲሆኑ ለሚወዱትም ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?