ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ፥ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወድዳቸዋል።
ለአንተ የተለየሁ ሰው ነኝና ነፍሴን ጠብቃት፤ አንተ አምላኬ ሆይ፤ በአንተ የታመነብህን ባሪያህን አድን።
ታማኝ ነኝና ነፍሴን ጠብቅ፥ አምላኬ ሆይ፥ በአንተ የታመነውን አገልጋይህን አድነው።
እኔ ለአንተ ታማኝ ስለ ሆንኩ ሕይወቴን ጠብቃት፤ አንተ አምላኬ ነህ፤ በአንተ የምታምነውን እኔን አገልጋይህን አድነኝ።
ከከንፈራቸው በታች የእባብ መርዝ አለ፤ አፋቸው መራራ ነው፥ መርገምንም ተሞልቶአል፤
ልጆቻቸው በጐልማስነታቸው እንደ አዲስ ተክል የሆኑ፥ ሴቶች ልጆቻቸውም እንደ እልፍኝ ያማሩና ያጌጡ፤
አቤቱ፥ ጽድቄን ስማኝ፥ ልመናዬንም አድምጠኝ፤ በተንኰለኛም ከንፈር ያልሆነውን ጸሎቴን አድምጠኝ፤
አቤቱ፥ ፈትነኝ መርምረኝም፤ ኵላሊቴንና ልቤን ፈትን።
ኀጢአታቸው የተተወላቸው፥ በደላቸውንም ሁሉ ያልቈጠረባቸው ብፁዓን ናቸው።
እግዚአብሔር በጻድቁ እንደ ተገለጠ ዕወቁ፤ እግዚአብሔር ወደ እርሱ በጮኽሁ ጊዜ ይሰማኛል።
እነሆ፥ በኀጢአት ተፀነስሁ፥ እናቴም በዐመፃ ወለደችኝ።
እኔን የሚያገለግለኝ ካለ ይከተለኝ፤ የሚያገለግለኝ እኔ ባለሁበት በዚያ ይኖራልና፤ እኔን የሚያገለግለኝንም አብ ያከብረዋል።
እንግዲህ በዓለም አልኖርም፤ እነርሱ ግን በዓለም ይኖራሉ፤ እኔም ወደ አንተ እመጣለሁ፤ ቅዱስ አባት ሆይ፥ እነዚህን የሰጠኸኝን እንደ እኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ በስምህ ጠብቃቸው፤
እነሆ፥ የሚወድደውን ይምረዋል፤ የሚወድደውንም ልቡን ያጸናዋል።
ለሚጸልይ ጸሎቱን ይሰጠዋል፤ የጻድቃንን ዘመን ይባርካል፤ የሰው ኀይል ጽኑዕ አይደለምና።