መዝሙር 86:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መሠረቶችዋ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ጆሮህን ወደ እኔ ጣል፤ ስማኝም፤ እኔ ችግረኛ ድኻ ነኝና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዳዊት ጸሎት አቤቱ፥ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል አድምጠኝም፥ ደሃና ችግረኛ ነኝና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ችግረኛና ድኻ ስለ ሆንኩ እባክህ ጸሎቴን ስማ፤ መልስም ስጠኝ። |
በጨነቀኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፥ ወደ አምላኬም ጮኽሁ፤ በቤተ መቅደሱም ቃሌን ሰማኝ፥ ጩኸቴም በፊቱ ወደ ጆሮው ገባ።
አቤቱ፥ ጆሮህን አዘንብልና ስማ፤ አቤቱ፥ ዐይንህን ክፈትና በሕያው አምላክ ላይ ይገዳደር ዘንድ የላከውን የሰናክሬምን ቃል ተመልከት።
ይህ ሁሉ የእጄ ሥራ ነው፤ ይህም ሁሉ የእኔ ነው፥” ይላል እግዚአብሔር፤ “ወደ የዋሁና ወደ ጸጥተኛው፥ ከቃሌም የተነሣ ወደሚንቀጠቀጥ ሰው ከአልሆነ በቀር ወደ ማን እመለከታለሁ?
“የእግዚአብሔር መንፈስ በላዬ ነው፤ ስለዚህ ቀብቶ ለድሆች የምሥራችን እነግራቸው ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን እሰብክላቸው ዘንድ፥ ያዘኑትንም ደስ አሰኛቸው ዘንድ፥ ዕውሮችም ያዩ ዘንድ፥ የተገፉትንም አድናቸው ዘንድ፥ የታሰሩትንም እፈታቸው ዘንድ፥ የቈሰሉትንም አድናቸው ዘንድ፥
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ባለ ጠጎች እንዲሆኑ ለሚወዱትም ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?