Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 86:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር ሆይ! ችግረኛና ድኻ ስለ ሆንኩ እባክህ ጸሎቴን ስማ፤ መልስም ስጠኝ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ጆሮህን ወደ እኔ ጣል፤ ስማኝም፤ እኔ ችግረኛ ድኻ ነኝና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የዳዊት ጸሎት አቤቱ፥ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል አድምጠኝም፥ ደሃና ችግረኛ ነኝና።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 መሠ​ረ​ቶ​ችዋ በተ​ቀ​ደሱ ተራ​ሮች ናቸው፤

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 86:1
19 Referencias Cruzadas  

አምላክ ሆይ! አንተ ግን ችግርንና ጭንቀትን አይተህ ልታስወግዳቸው መፍትሔ ታዘጋጃለህ፤ ችግረኛ ራሱን ለአንተ ይሰጣል፤ አንተም የሙት ልጆችን ትረዳለህ።


እግዚአብሔር ሆይ! ጸሎቴን ስማ! የአንተን ርዳታ በመፈለግ ስጮኽም አድምጠኝ!


የድኾችን ጸሎት ይሰማል፤ ልመናቸውንም አይንቅም።


እኔ ሕግህን ስለ ጠበቅሁ ስድባቸውንና ንቀታቸውን ከእኔ አርቅልኝ።


እግዚአብሔር ሆይ! ለድኾች እንደምትፈርድ፥ ለተጨቈኑትም መብታቸውን እንደምታስከብር ዐውቃለሁ።


ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ፤ ምሕረት እንዲያደርግልኝ እለምነዋለሁ።


አምላክ ሆይ! ልመናዬን ስለምትሰማ፥ ወደ አንተ እጸልያለሁ፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ ቃሌንም ስማ።


እኔ ብቸኛና ችግረኛ ስለ ሆንኩ አምላክ ሆይ! ወደ እኔ ተመለስ፤ በጎነትንም አድርግልኝ።


ጌታ ሆይ! አድምጠኝ፤ ፈጥነህም በመምጣት አድነኝ፤ መጠጊያ አለትና ጠንካራ ምሽግ ሆነህ አድነኝ።


ይህ ድኻ ሰው ተጣራ፤ እግዚአብሔርም ሰማው፤ ከችግሩም ሁሉ አዳነው።


አምላክ ሆይ! እኔ ችግረኛ ድኻ ነኝ፤ አንተ ግን አልረሳኸኝም፤ አንተ ረዳቴና አዳኜ ስለ ሆንክ አሁንም በፍጥነት እርዳኝ።


አምላክ ሆይ! ሰናክሬም! እንዴት አድርጎ አንተን ሕያው አምላክን እንደ ዘለፈ ተመልከት።


እነዚህን ሁሉ ነገሮች የፈጠርኩ እኔ ነኝ፤ ስለዚህ ሁሉም የእኔ ናቸው፤ እኔ የምመለከተው ልባቸው ወደ ተሰበረ፥ ትሑት መንፈስ ወዳላቸውና፥ ቃሌንም ወደሚያከብሩ ነው።


አምላክ ሆይ! እባክህ አድምጠኝ፤ የእኛን ችግርና በስምህ የምትጠራውን ከተማ ጥፋት ተመልከት፤ ወደ አንተ የምንጸልየው የአንተን ምሕረት በመተማመን እንጂ በእኛ መልካም ሥራ በመመካት አይደለም።


“መንግሥተ ሰማይ የእነርሱ ስለ ሆነች በመንፈሳዊ ኑሮአቸው ድኾች መሆናቸው የሚሰማቸው የተባረኩ ናቸው።


“የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ መልካም ዜናን ለድኾች እንዳበሥር ሾሞኛል፤ ለታሰሩት መፈታትን፥ ለዕውሮች ማየትን እንዳውጅና የተጨቈኑትንም ነጻ እንዳወጣ ልኮኛል፤


የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ሀብታሞች እንዲሆኑና እርሱን ለሚወዱት ተስፋ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos