መዝሙር 85:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምሕረትህ በእኔ ላይ ታላቅ ናትና፥ ነፍሴንም ከታችኛዪቱ ሲኦል አድነሃታልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጽድቅ በፊቱ ይሄዳል፤ ለአረማመዱም መንገድ ያዘጋጃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም በጎ ነገርን ይሰጣል፥ ምድራችንም ፍሬዋን ትሰጣለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፈለጉን እንከተል ዘንድ ጽድቅ በእግዚአብሔር ፊት ይሄዳል። |
ያን ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል፤ ፈውስህም ፈጥኖ ይወጣል፤ ጽድቅህም በፊትህ ይሄዳል፤ የእግዚአብሔርም ክብር ይጋርድሃል።
የካህናቱንም የሌዊን ልጆች ሰውነት ከፍ ከፍ አደርጋታለሁ፤ አረካታለሁ፤ ሕዝቤም ከበረከቴ ይጠግባል፥” ይላል እግዚአብሔር።
“እርስ በርሳችሁ ቷደዱ ዘንድ፥ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እንዲሁ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ።
እኛስ ሁላችን ፊታችንን ገልጠን በመስተዋት እንደሚያይ የእግዚአብሔርን ክብር እናያለን፤ ከእግዚአብሔር መንፈስ እንደ ተሰጠን መጠን የእርሱን አርአያ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንገባለን።
ከክርስቶስ ጋርም ተሰቀልሁ፤ ሕይወቴም አለቀች፤ ነገር ግን በክርስቶስ ሕይወት አለሁ፤ ዛሬም በሥጋዬ የምኖረውን ኑሮ የወደደኝን ስለ እኔም ራሱን አሳልፎ የሰጠውን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመን እኖራለሁ።
ክርስቶስም በሥጋ ስለ እኛ መከራን ስለተቀበለ፥ ከእንግዲህ ወዲህ በሥጋ ልትኖሩ በቀረላችሁ ዘመን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ እንደ ሰው ምኞት እንዳትኖሩ፥ እናንተ ደግሞ ያን አሳብ እንደ ዕቃ ጦር አድርጋችሁ ያዙት፤ በሥጋ መከራን የተቀበለ ኀጢአትን ትቶአልና።