መዝሙር 80:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠላቶቻቸውን ፈጥኜ ባዋረድኋቸው ነበር፥ በሚያስጨንቋቸውም ላይ እጄን በጣልሁ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰራዊት አምላክ ሆይ፤ እንግዲህ ወደ እኛ ተመለስ፤ ከሰማይ ተመልከት፤ እይም፤ ይህችን የወይን ተክል ተንከባከባት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዱር እርያ አረከሳት፥ የአገር አውሬም ተሰማራባት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሠራዊት አምላክ ሆይ! ፊትህን ወደ እኛ መልስ! ከሰማይ ወደ እኛ ወደ ታች ተመልከት፤ እይም፤ ይህን የወይን ግንድህን ጠብቅ! |
ከሰማይ ተመለስ፤ ከቅድስናህና ከክብርህ ማደሪያም ተመልከት፤ ቅንአትህና ኀይልህስ ወዴት ነው? የቸርነትህና የይቅርታህ ብዛት ወዴት ነው? ቸል ብለሃልና።
አቤቱ፥ ከመንገድህ ለምን አሳትኸን? እንዳንፈራህም ልባችንን ለምን አጸናህብን? ስለ ባሪያዎችህ ስለ ርስትህ ነገዶች ተመለስ፤
የሚመለስና የሚጸጸት እንደ ሆነ፥ ለአምላካችሁም ለእግዚአብሔር የእህልና የመጠጥ ቍርባን የሚሆን በረከትን በኋላ የሚያተርፍ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?
ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከሥርዓቴ ፈቀቅ ብላችኋል፥ እርስዋንም አልጠበቃችሁም። ወደ እኔ ተመለሱ፥ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተ ግን፦ የምንመለሰው በምንድር ነው? ብላችኋል።