እግዚአብሔርም በእስራኤል ዘር ሁሉ ተቈጣ፤ አስጨነቃቸውም፤ ከፊቱም እስኪጥላቸው ድረስ በበዝባዦች እጅ አሳልፎ ሰጣቸው።
መዝሙር 80:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቤስ ቃሌን ሰምተውኝ ቢሆን፥ እስራኤልም በመንገዴ ሄደው ቢሆን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕሪያ ከዱር ወጥቶ ያበለሻሻታል፤ በሜዳ የሚንጋጋ እንስሳ ሁሉ ይበላታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አጥርዋን ለምን አፈረስህ? መንገድ አላፊም ሁሉ ይቀጥፋታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዱር እርያዎች ይረጋግጡአታል፤ የበረሓ አራዊትም ይመገቡአታል። |
እግዚአብሔርም በእስራኤል ዘር ሁሉ ተቈጣ፤ አስጨነቃቸውም፤ ከፊቱም እስኪጥላቸው ድረስ በበዝባዦች እጅ አሳልፎ ሰጣቸው።
አሁንም በወይኔ ላይ የማደርገውን እነግራችኋለሁ፤ አጥሩን እነቅላለሁ፤ ለብዝበዛም ይሆናል፤ ቅጥሩንም አፈርሳለሁ፤ ለመራገጫም ይሆናል።
አንበሳ ከጕድጓዱ ወጥቶአል፤ አሕዛብንም ሊያጠፋቸው የሚዘርፍ ተነሥቶአል፤ ምድርሽን ባድማ ያደርግ ዘንድ፥ ከተሞችሽንም ሰው እንዳይኖርባቸው ያፈርሳቸው ዘንድ ከስፍራው ወጥቶአል።
ስለዚህ ኀጢአታቸው በዝቶአልና፥ የዐመፃቸውም ብዛት ጸንቶአልና አንበሳ ከዱር ወጥቶ ይሰብራቸዋል፤ የበረሃም ተኵላ ያጠፋቸዋል፥ ነብርም በከተሞቻቸው ላይ ይተጋል፤ ከዚያም የሚወጣ ሁሉ ይነጠቃል።
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በላኝ፤ ከፋፈለኝም፤ እንደ ባዶ ዕቃም አደረገኝ፤ እንደ ዘንዶም ዋጠኝ፤ ከሚጣፍጠውም ሥጋዬ ሆዱን ሞላ።
ከተማዪቱም ተሰበረች፤ ሰልፈኞችም ሁሉ ሸሹ፤ በሁለቱም ቅጥር መካከል ባለው በር ወደ ንጉሥ አትክልት በሚወስደው መንገድ በሌሊት ከከተማዪቱ ወጡ። ከለዳውያንም በከተማዪቱ ዙሪያ ነበሩ፤ በዓረባም መንገድ ሄዱ።
ነገር ግን በመዓት ተነቀለች፤ ወደ መሬትም ተጣለች፤ የሚያቃጥልም ነፋስ ፍሬዋን አደረቀ፤ ብርቱዎች በትሮችዋም ተሰበሩና ደረቁ፤ እሳትም በላቻቸው።
የኃያላኑ ጋሻ ቀልቶአል፥ ጽኑዓንም ቀይ ልብስ ለብሰዋል። እርሱም በሚያዘጋጅበት ቀን ሰረገሎች እንደ እሳት ይንቦገቦጋሉ፣ የጦሩም ሶመያ ይወዛወዛል።