የባሪያዎችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ፥ የጻድቃንህንም ሥጋ ለምድር አራዊት፤
አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ፤ ከጥንት በነበረ እንቈቅልሽ እናገራለሁ፤
አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ፥ ከቀድሞ ጀምሮ ያለውንም እንቆቅልሽ እናገራለሁ።
ንግግሬን በምሳሌ እጀምራለሁ፤ ከጥንት ጀምሮ የተሰወረውን ምሥጢር እገልጣለሁ።
በላይ ያለውን ሰማይን ምድርንም በሕዝቡ ለመፍረድ ይጠራል፥
እንደ ሕጉ መሥዋዕትን የሚያቀርቡትን፥ ጻድቃኑን ሰብስቡለት።
ምሳሌንና የተሸሸገውን ነገር፥ የጠቢባንን ቃልና ዕንቈቅልሾችን ያውቃል።
እኔ አምላክ ነኝና፤ ያለ እኔም ሌላ የለምና የቀድሞውንና የጥንቱን ነገር ዐስቡ። እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም።
ለብቻቸውም ሲሆኑ ነገሩን ሁሉ ለገዛ ደቀ መዛሙርቱ ይፈታላቸው ነበር።
ዛሬም እንዳሉ እግዚአብሔር በቍጣና በመቅሠፍት፥ በታላቅም መዓት ከምድራቸው ነቀላቸው፤ ወደ ሌላም ምድር ጣላቸው።