መዝሙር 78:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛ ሕዝብህ ግን፥ የማሰማሪያህም በጎች፥ ለዘለዓለም እናመሰግንሃለን፤ ለልጅ ልጅም ምስጋናህን እንናገራለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባሕሩን ከፍሎ አሻገራቸው፤ ውሃውንም እንደ ክምር አቆመ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባሕርን ከፍሎ አሳለፋቸው፥ ውኆችን እንደ ግንብ አቆመ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባሕሩን ከፍሎ በመካከሉ አሳለፋቸው፤ ውሃው እንደ ግንብ እንዲቆም አደረገ። |
ሙሴም በባሕሩ ላይ እጁን ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ሌሊቱን ሁሉ ጽኑ የአዜብ ነፋስ አምጥቶ ባሕሩን አስወገደው፤ ባሕሩንም አደረቀው፤ ውኃውም ተከፈለ።
እንዲህም ይሆናል፤ የምድርን ሁሉ ጌታ የእግዚአብሔርን ታቦት የተሸከሙ ካህናት እግር ጫማ በዮርዳኖስ ውኃ ውስጥ ሲቆም፥ የዮርዳኖስ ውኃ ይደርቃል፤ ከላይ የሚወርደውም ውኃ ይቆማል።”
ከላይ የሚወርደው ውኃ ቆመ፤ እስከ ቀርያትያርም አውራጃ እጅግ ርቆ እንደ ግድግዳ ቆመ፤ ወደ ዓረባ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚወርደው ውኃም ፈጽሞ ደረቀ፤ ሕዝቡም በኢያሪኮ ፊት ለፊት ቆሙ።