ባሕርን ከፍሎ አሳለፋቸው፤ ውኆችን እንደ ረዋት ውኃ አቆመ።
አምላክ ሆይ፤ መንገድህ ቅዱስ ነው፤ እንደ አምላካችን ያለ ታላቅ አምላክ ማን ነው?
በምግባርህም ሁሉ እናገራለሁ፥ ሥራህንም አሰላስላለሁ።
አምላክ ሆይ፥ አንተ የምታደርገው ሁሉ ቅዱስ ነው፤ እንደ አንተ ያለ ታላቅ አምላክ ማነው?
የእግዚአብሔርን ኀይል ማን ይናገራል? ምስጋናውንስ ሁሉ ይሰማ ዘንድ ማን ያደርጋል?
እንደ ሥራቸውና እንደ ዐሳባቸው ክፋት ስጣቸው፤ እንደ እጃቸውም ሥራ ክፈላቸው፤ ፍዳቸውን በራሳቸው ላይ መልስ።
ከክፉዎች ሴራ ከብዙዎች ዐመፅ አድራጊዎች ሰውረኝ።
ከተማቸው በረሃ ትሁን፥ በድንኳኖቻቸውም የሚቀመጥ አይገኝ፤
የምስጋናው ስም ለዓለምና ለዘለዓለም ይባረክ፤ ምስጋናውም ምድርን ሁሉ ይምላ። ይሁን፤ ይሁን።
አንተ የምድር ዳርቻዎችን ሁሉ ሠራህ፤ በጋንና ክረምትን አንተ አደረግህ።
አቤቱ፦ በአማልክት መካከል አንተን የሚመስል ማን ነው? በቅዱሳንም ዘንድ እንደ አንተ የከበረ ማን ነው? በምስጋና የተደነቅህ ነህ፤ ድንቅንም የምታደርግ ነህ፤
እንግዲህ እግዚአብሔርን በማን ትመስሉታላችሁ? ወይስ በምን ምሳሌ ታስተያዩታላችሁ?
እንግዲህ እተካከለው ዘንድ በማን መሰላችሁኝ? ይላል ቅዱሱ እግዚአብሔር።
እንግዲህ በማን ትመስሉኛላችሁ? የምትሳሳቱ እናንተ ሁላችሁ፥ እዩ፤ አስተውሉም።
አምላካችን እንደ አምላኮቻቸው አይደለምና፤ ጠላቶቻችንም ሰነፎች ናቸው።