አሁንም እንደ አባቶቻችሁ አንገታችሁን አታደንድኑ፤ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ምስጋና ስጡ፤ ለዘለዓለምም ወደ ተቀደሰው ወደ መቅደሱ ግቡ፤ ጽኑ ቍጣውንም ከእናንተ እንዲመልስ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ተገዙ።
መዝሙር 75:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልበ ሰነፎች ሁሉ ደነገጡ፥ ሕልምን አለሙ፥ ያገኙት ግን የለም፤ ሰው ሁሉ ለእጁ ባለጠግነት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀንድህን ወደ ሰማይ አታንሣ፤ ዐንገትህንም መዝዘህ አትናገር።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትምክህተኞችን፦ “አትኩሩ፥ ክፉዎችንም፦ ቀንዳችሁን አታንሡ፥” አልኋቸው አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእግዚአብሔር ላይ ራስህን ከፍ ከፍ አታድርግ፤ ወይም በትዕቢት አትናገር።” |
አሁንም እንደ አባቶቻችሁ አንገታችሁን አታደንድኑ፤ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ምስጋና ስጡ፤ ለዘለዓለምም ወደ ተቀደሰው ወደ መቅደሱ ግቡ፤ ጽኑ ቍጣውንም ከእናንተ እንዲመልስ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ተገዙ።
እነርሱ ፊታቸው የከፋ፥ ልባቸው የደነደነ ልጆች ናቸው። እኔ ወደ እነርሱ እልክሃለሁ፤ አንተም፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል በላቸው።
“እናንተ አንገታችሁ የደነደነ፥ ልባችሁም የተደፈነ፥ ጆሮአችሁም የደነቈረ፥ እንደ አባቶቻችሁ መንፈስ ቅዱስን ዘወትር ትቃወማላችሁ።
እኔ ዐመፃችሁንና የአንገታችሁን ድንዳኔ አውቃለሁና፤ እኔም ዛሬ ከእናንተ ጋር ገና በሕይወት ሳለሁ እናንተ በእግዚአብሔር ላይ ዐምፃችኋል፤ ይልቁንስ ከሞትሁ በኋላ እንዴት ይሆናል?