በጽድቅህ አስጥለኝ፥ ታደገኝም፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፥ ፈጥነህም አድነኝ።
ነፍሴን ለመንጠቅ የሚፈልጉ፣ ይፈሩ፤ ይዋረዱም፤ ጕዳቴንም የሚሹ፣ ተዋርደው በመጡበት ይመለሱ።
አቤቱ፥ አድነኝ፥ አቤቱ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
ሊገድሉኝ የሚፈልጉ ሁሉ ይፈሩ ግራም ይጋቡ፤ የእኔን ጒዳት የሚመኙ ሁሉ በውርደት ወደ ኋላቸው ይመለሱ።
በቃሌ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፤ በቃሌ ወደ እግዚአብሔር ለመንሁ።
በመኝታው ዐመፅን ዐሰበ፤ በሁሉ ነገር መልካም ባልሆነች መንገድ ቆሞአል፤ ክፋትንም አይሰለቻትም።
ጠላቶቼ ሁሉ ይፈሩ፥ ይጐስቁሉም፤ ወደ ኋላቸው ይመለሱ፥ በፍጥነትም እጅግ ይፈሩ።
ድሃውን ከሚቀማው እጅ፥ ረዳት የሌለውንም ምስኪን ያድነዋልና።
ለድሃና ለምስኪን ይራራል፥ የድሆችንም ነፍስ ያድናል።
ስለዚህ ሄደው ወደ ኋላ እንዲወድቁ፥ እንዲሰበሩም፥ ተጠምደውም እንዲቸገሩ፥ የግዚአብሔርም ቃሉ በሕማም ላይ ሕማም፥ በተስፋ ላይ ተስፋ፥ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ ይሆንላቸዋል።
እነሆ፥ የሚቃወሙህ ሁሉ ያፍራሉ፤ ይዋረዱማል፤ እንዳልነበሩም ይሆናሉ፤ ጠላቶችህም ይጠፋሉ።
ጌታችን ኢየሱስም፥ “እኔ ነኝ” ባላቸው ጊዜ፤ ወደ ኋላቸው ተመልሰው በምድር ላይ ወደቁ።