Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 28:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ስለ​ዚህ ሄደው ወደ ኋላ እን​ዲ​ወ​ድቁ፥ እን​ዲ​ሰ​በ​ሩም፥ ተጠ​ም​ደ​ውም እን​ዲ​ቸ​ገሩ፥ የግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃሉ በሕ​ማም ላይ ሕማም፥ በተ​ስፋ ላይ ተስፋ፥ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል፣ በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፣ በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፤ በደንብ ላይ ደንብ፣ በደንብ ላይ ደንብ፤ እዚህ ጥቂት እዚያ ጥቂት ይሆንባቸዋል። ይህ የሚሆንባቸው ሄደው ወደ ኋላ እንዲወድቁ፣ እንዲቈስሉና በወጥመድ እንዲያዙ፣ እንዲማረኩም ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ስለዚህ ሄደው ወደ ኋላ እንዲወድቁ፥ እንዲሰበሩም፥ በወጥመድም እንዲያዙ፥ የጌታ ቃል በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፥ በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፥ በደንብ ላይ ደንብ፥ በደንብ ላይ ደንብ፤ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ ይሆንላቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እግዚአብሔር ፊደል በፊደል ላይ፥ መስመር በመስመር ላይ፥ ትምህርት በትምህርት ላይ እያነባበረ ሊያስተምራችሁ የፈቀደው ስለዚህ ነው፤ በዚያን ጊዜ በእርምጃችሁ ሁሉ ትሰናከላላችሁ፤ ትቈስላላችሁ፤ በወጥመድም ተይዛችሁ ትታሰራላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ስለዚህ ሄደው ወደ ኋላ እንዲወድቁ እንዲሰበሩም ተጠምደውም እንዲያዙ የእግዚአብሔር ቃል ትእዛዝ በትእዛዝ፥ ትእዛዝ በትእዛዝ፥ ሥርዓት በሥርዓት፥ ሥርዓት በሥርዓት፥ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ ይሆንላቸዋል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 28:13
14 Referencias Cruzadas  

ሕማ​ምን በሕ​ማም ላይ፥ ተስ​ፋ​ንም በተ​ስፋ ላይ ተቀ​በሉ፤ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ ነው።


እንደ ዕው​ሮች ወደ ቅጥሩ ተር​መ​ሰ​መሱ፤ ዐይ​ንም እን​ደ​ሌ​ላ​ቸው ተር​መ​ሰ​መሱ፤ በቀ​ት​ርም ጊዜ በመ​ን​ፈቀ ሌሊት እን​ዳለ ሰው ተሰ​ና​ከሉ፤ እንደ ሙታ​ንም ይጨ​ነ​ቃሉ።


ስለ​ዚህ ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ች​ሁን አጨ​ድ​ኋ​ቸው፤ በአ​ፌም ቃል ገደ​ል​ኋ​ቸው፤ ፍር​ዴም እንደ ብር​ሃን ይወ​ጣል።


ብዙ ሕጎ​ችን እጽ​ፍ​ለ​ታ​ለሁ፤ ነገር ግን ሥር​ዐ​ቱና የተ​ወ​ደ​ደው መሠ​ዊ​ያው እንደ እን​ግዳ ነገር ተቈ​ጠሩ።


‘መስማት ትሰማላችሁና አታስተውሉም፤ ማየትም ታያላችሁና አትመለከቱም።


በዚህም ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ይቀጠቀጣል፤ ድንጋዩ ግን የሚወድቅበትን ሁሉ ይፈጨዋል።”


ዳዊ​ትም እን​ዲህ ብሎ​አል፥ “ማዕ​ዳ​ቸው በፊ​ታ​ቸው ወጥ​መ​ድና አሽ​ክላ፥ መሰ​ና​ከ​ያና ፍዳም ትሁ​ን​ባ​ቸው።


የሞት መዓዛ የሚ​ገ​ባ​ቸው ለሞት፥ የሕ​ይ​ወት መዓዛ የሚ​ገ​ባ​ቸ​ውም ለሕ​ይ​ወት ናቸው፤ ነገር ግን ይህ የሚ​ገ​ባው ማነው?


በመልእክቱም ሁሉ ደግሞ እንደ ነገረ ስለዚህ ነገር ተናገረ። በእነዚያ ዘንድ ለማስተዋል የሚያስቸግር ነገር አለ፤ ያልተማሩትና የማይጸኑትም ሰዎች ሌሎችን መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ እነዚህን ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos