እኔ ድሃና ምስኪን ነኝ፤ እግዚአብሔርም ይረዳኛል፤ ረዳቴ መጠጊያዬም አንተ ነህ፥ አቤቱ አምላኬ አትዘግይ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ቂልነቴን ታውቃለህ፤ በደሌም ከአንተ የተሰወረ አይደለም።
በከንቱ የሚጠሉኝ ከራሴ ጠጉር በዙ፥ በዓመፅ ያሚያሳድዱኝ ጠላቶቼ በረቱ፥ በዚያን ጊዜ ያልቀማሁትን መለስሁ።
አምላክ ሆይ! ሞኝነቴን አንተ ታውቃለህ፤ ኃጢአቴ ከአንተ የተሰወረ አይደለም።
እግዚአብሔርን በጠራሁት ጊዜ ከጠላቶቼ እድናለሁ።
እነሆ፥ ዘመኖቼን አስረጀሃቸው፤ አካሌም በፊትህ እንደ ኢምንት ነው። ነገር ግን የሰው ልጅ ሁሉ ከንቱ ነው።
ዝም አልሁ አፌንም አልከፈትሁም። አንተ ፈጥረኸኛልና፤
ዐይኖች በመንገዳቸው ሁሉ ይመለከታሉ፤ ከፊቴም አልተሰወሩም፤ ኀጢአታቸውም ከዐይኖች አልተሸሸገም።