እኛ ሕዝብህ ግን፥ የማሰማሪያህም በጎች፥ ለዘለዓለም እናመሰግንሃለን፤ ለልጅ ልጅም ምስጋናህን እንናገራለን።
መዝሙር 66:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድር ፍሬዋን ሰጠች፤ እግዚአብሔር አምላካችንም ይባርከናል፥ የምድርም ዳርቻ ሁሉ ይፈሩታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባሕሩን የብስ አደረገው፤ ወንዙን በእግር ተሻገሩ፤ ኑ፣ በርሱ ደስ ይበለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባሕርን የብስ አደረጋት፥ ወንዙንም በእግር ተሻገሩ፥ በዚያ በእርሱ ደስ ይለናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ባሕሩን ወደ ደረቅ መሬት ለውጦአል፤ የቀድሞ አባቶቻችን ወንዙን በእግር ተሻግረዋል፤ እኛም እርሱ ባደረገው ነገር ደስ ብሎናል። |
እኛ ሕዝብህ ግን፥ የማሰማሪያህም በጎች፥ ለዘለዓለም እናመሰግንሃለን፤ ለልጅ ልጅም ምስጋናህን እንናገራለን።
እንዲህም ሆነ፤ ሕዝቡ ዮርዳኖስን ሊሻገሩ ከየድንኳናቸው በወጡ ጊዜ፥ የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት በሕዝቡ ፊት ይሄዱ ነበር።
ከላይ የሚወርደው ውኃ ቆመ፤ እስከ ቀርያትያርም አውራጃ እጅግ ርቆ እንደ ግድግዳ ቆመ፤ ወደ ዓረባ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚወርደው ውኃም ፈጽሞ ደረቀ፤ ሕዝቡም በኢያሪኮ ፊት ለፊት ቆሙ።
የእግዚአብሔርንም የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት በዮርዳኖስ መካከል በደረቅ መሬት ጸንተው ቆመው ነበር፤ ሕዝቡም ሁሉ ዮርዳኖስን ፈጽመው እስኪሻገሩ ድረስ የእስራኤል ልጆች ሁሉ በደረቅ መሬት ተሻገሩ።