Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 78:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እኛ ሕዝ​ብህ ግን፥ የማ​ሰ​ማ​ሪ​ያ​ህም በጎች፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እና​መ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለን፤ ለልጅ ልጅም ምስ​ጋ​ና​ህን እን​ና​ገ​ራ​ለን።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ባሕሩን ከፍሎ አሻገራቸው፤ ውሃውንም እንደ ክምር አቆመ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ባሕርን ከፍሎ አሳለፋቸው፥ ውኆችን እንደ ግንብ አቆመ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ባሕሩን ከፍሎ በመካከሉ አሳለፋቸው፤ ውሃው እንደ ግንብ እንዲቆም አደረገ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 78:13
15 Referencias Cruzadas  

አሁ​ንስ ተስ​ፋዬ ማን ነው? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ምን? ትዕ​ግ​ሥ​ቴም ከአ​ንተ ዘንድ ነው።


ምድር ፍሬ​ዋን ሰጠች፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ች​ንም ይባ​ር​ከ​ናል፥ የም​ድ​ርም ዳርቻ ሁሉ ይፈ​ሩ​ታል።


ሙሴም በባ​ሕሩ ላይ እጁን ዘረጋ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሌሊ​ቱን ሁሉ ጽኑ የአ​ዜብ ነፋስ አም​ጥቶ ባሕ​ሩን አስ​ወ​ገ​ደው፤ ባሕ​ሩ​ንም አደ​ረ​ቀው፤ ውኃ​ውም ተከ​ፈለ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በባ​ሕሩ መካ​ከል በየ​ብስ ገቡ፤ ውኃ​ውም በቀ​ኛ​ቸ​ውና በግ​ራ​ቸው እንደ ግድ​ግዳ ሆነ​ላ​ቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ግን በባ​ሕሩ ውስጥ በየ​ብስ ሄዱ፤ ውኃ​ውም በቀ​ኛ​ቸ​ውና በግ​ራ​ቸው እንደ ግድ​ግዳ ሆነ​ላ​ቸው።


በቍ​ጣህ እስ​ት​ን​ፋስ ውኃው ቆመ፤ ውኃ​ዎች እንደ ግደ​ግዳ ቆሙ፤ ሞገ​ዱም በባ​ሕር መካ​ከል ረጋ።


በሙ​ሴም ቀኝ እጅ ውኃ​ውን ከፈ​ልሁ፤” ውኃ​ውም ተከ​ፍሎ በፊቱ ጸና፤ የዘ​ለ​ዓ​ለም ስም​ንም አደ​ረ​ገ​ለት።


ፈረስ በም​ድረ በዳ እን​ደ​ሚ​ያ​ልፍ፥ በቀ​ላይ ውስጥ አሳ​ለ​ፋ​ቸው፥ እነ​ር​ሱም አል​ደ​ከ​ሙም።


ፈረሶችህን በባሕር፥ በብዙ ውኆችም ላይ አስረገጥህ።


እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ የም​ድ​ርን ሁሉ ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት እግር ጫማ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ውኃ ውስጥ ሲቆም፥ የዮ​ር​ዳ​ኖስ ውኃ ይደ​ር​ቃል፤ ከላይ የሚ​ወ​ር​ደ​ውም ውኃ ይቆ​ማል።”


ከላይ የሚ​ወ​ር​ደው ውኃ ቆመ፤ እስከ ቀር​ያ​ት​ያ​ርም አው​ራጃ እጅግ ርቆ እንደ ግድ​ግዳ ቆመ፤ ወደ ዓረባ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚ​ወ​ር​ደው ውኃም ፈጽሞ ደረቀ፤ ሕዝ​ቡም በኢ​ያ​ሪኮ ፊት ለፊት ቆሙ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos