Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢያሱ 4:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ለል​ጆ​ቻ​ችሁ እን​ዲህ ብላ​ችሁ ትነ​ግ​ሯ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ፦ ‘እስ​ራ​ኤል ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስን በደ​ረቅ ተሻ​ገረ፤’

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ‘እስራኤል ይህን ዮርዳኖስ በደረቅ ምድር ተሻገረ’ ብላችሁ ንገሯቸው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ለልጆቻችሁ እንዲህ ብላችሁ ታስታውቃላችሁ፦ ‘እስራኤል ይህን ዮርዳኖስን በደረቅ ምድር ላይ ተሻገረ፤’

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 የእስራኤል ሕዝብ የዮርዳኖስን ወንዝ በደረቅ ምድር የተሻገሩበት ጊዜ መኖሩን ትነግሩአቸዋላችሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ለልጆቻችሁ እንዲህ ብላችሁ ታስታውቃላችሁ፦ እስራኤል ይህን ዮርዳኖስን በደረቅ ተሻገረ፥

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 4:22
11 Referencias Cruzadas  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት በዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል በደ​ረቅ መሬት ጸን​ተው ቆመው ነበር፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ፈጽ​መው እስ​ኪ​ሻ​ገሩ ድረስ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ በደ​ረቅ መሬት ተሻ​ገሩ።


ባሕ​ሩን ያደ​ረ​ቅሽ፥ ጥል​ቁ​ንም ውኃ ያደ​ረ​ቅ​ሽው፥ የዳ​ኑ​ትም ይሻ​ገሩ ዘንድ ጥል​ቁን ባሕር ጥር​ጊያ ጎዳና ያደ​ረ​ግሽ አይ​ደ​ለ​ሽ​ምን?


ስድስተኛውም ጽዋውን በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከፀሐይም መውጫ ለሚመጡ ነገሥታት መንገድ እንዲሰናዳላቸው ውሃው ደረቀ።


ቀላ​ይ​ዋ​ንም፥ “ደረቅ ሁኚ ፈሳ​ሾ​ች​ሽም ይድ​ረቁ” ይላል፤


“የፈ​ር​ዖን ፈረ​ሶች ከሰ​ረ​ገ​ሎ​ቹና ከፈ​ረ​ሰ​ኞቹ ጋር ወደ ባሕር ገቡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የባ​ሕ​ሩን ውኆች መለ​ሰ​ባ​ቸው፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ግን በባ​ሕሩ መካ​ከል በየ​ብስ አለፉ፤ ውኃ​ውም ለእ​ነ​ርሱ በቀኝ እንደ ግድ​ግዳ፥ በግ​ራም እንደ ግድ​ግዳ ሆነ​ላ​ቸው።”


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ግን በባ​ሕሩ ውስጥ በየ​ብስ ሄዱ፤ ውኃ​ውም በቀ​ኛ​ቸ​ውና በግ​ራ​ቸው እንደ ግድ​ግዳ ሆነ​ላ​ቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በባ​ሕሩ መካ​ከል በየ​ብስ ገቡ፤ ውኃ​ውም በቀ​ኛ​ቸ​ውና በግ​ራ​ቸው እንደ ግድ​ግዳ ሆነ​ላ​ቸው።


ኢያ​ሱም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፥ “ልጆ​ቻ​ችሁ፦ ‘እነ​ዚህ ድን​ጋ​ዮች ምን​ድን ናቸው?’ ብለው በሚ​ጠ​ይ​ቋ​ችሁ ጊዜ፥


ከላይ የሚ​ወ​ር​ደው ውኃ ቆመ፤ እስከ ቀር​ያ​ት​ያ​ርም አው​ራጃ እጅግ ርቆ እንደ ግድ​ግዳ ቆመ፤ ወደ ዓረባ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚ​ወ​ር​ደው ውኃም ፈጽሞ ደረቀ፤ ሕዝ​ቡም በኢ​ያ​ሪኮ ፊት ለፊት ቆሙ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios