La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 62:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ንጉሥ ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይለ​ዋል፤ በእ​ር​ሱም የሚ​ምል ሁሉ ይከ​ብ​ራል፥ ዐመ​ፅን የሚ​ና​ገር አፍ ይዘ​ጋ​ልና።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር አንድ ነገር ተናገረ፤ እኔም ይህን ሁለት ጊዜ ሰማሁ፤ ኀይል የእግዚአብሔር ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዓመፃን ተስፋ አታድርጉ፥ ቅሚያንም አትተማመኑት፥ ባለጠግነት ቢበዛ ልባችሁ አይኩራ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ተናግሮአል፤ ኀይል የእግዚአብሔር መሆኑን ሁለት ጊዜ ሰምቼአለሁ።

Ver Capítulo



መዝሙር 62:11
12 Referencias Cruzadas  

ሕዝ​ቅ​ያ​ስም በእ​ነ​ርሱ ደስ አለው፤ ግምጃ ቤቱ​ንም ሁሉ፥ ብሩ​ንና ወር​ቁ​ንም፥ ሽቱ​ው​ንና የከ​በ​ረ​ው​ንም ዘይት፥ መሣ​ሪ​ያም ያለ​በ​ትን ቤት በቤተ መዛ​ግ​ብ​ቱም የተ​ገ​ኘ​ውን ሁሉ አሳ​ያ​ቸው፤ በቤ​ቱና በግ​ዛቱ ሁሉ ካለው ሕዝ​ቅ​ያስ ያላ​ሳ​ያ​ቸው የለም።


እር​ሱም፥ “ምን አዩ?” አለው ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፥ “በቤቴ ያለ​ውን ሁሉ አይ​ተ​ዋል፤ በቤተ መዛ​ግ​ብ​ቴም ካለው ያላ​ሳ​የ​ኋ​ቸው የለም” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ልም ወይም በሌ​ሊት ራእይ፥ አንድ ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ የተ​ና​ገረ እን​ደ​ሆነ፥


አንድ ጊዜ ተና​ገ​ርሁ፥ ሁለ​ተኛ ጊዜም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አል​ና​ገ​ርም።”


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዘ​ለ​ዓ​ለም አንባ ነውና ለዘ​ለ​ዓ​ለም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመኑ።


በታ​ላቅ ጥበ​ብ​ህና በን​ግ​ድህ ብል​ጽ​ግ​ና​ህን አብ​ዝ​ተ​ሃል፤ በብ​ል​ጽ​ግ​ና​ህም ልብህ ኰር​ቶ​አል።


ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ።


ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን።’


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ከሰ​ማይ ካል​ተ​ሰ​ጠህ በቀር በእኔ ላይ አን​ዳች ሥል​ጣን የለ​ህም፤ ስለ​ዚህ ለአ​ንተ አሳ​ልፎ የሰ​ጠኝ ሰው ታላቅ ኀጢ​ኣት አለ​በት” አለው።


ከዚህ በኋላ በሰማይ “ሃሌ ሉያ! በዝሙትዋ ምድርን ያጠፋችይቱን ታላቂቱን ጋለሞታ ስለ ፈረደባት፥ የባሪያዎቹንም ደም ከእጅዋ ስለ ተበቀለ፥ ፍርዶቹ እውነትና ጽድቅ ናቸውና ማዳንና ክብር ኀይልም የአምላካችን ነው፤” ብሎ ሲናገር እንደ ብዙ ሕዝብ ታላቅ ድምፅ ያለ ድምፅን ሰማሁ።