አቤቱ፥ በቍጣህ አትቅሠፈኝ፥ በመቅሠፍትህም አትገሥጸኝ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ በቍጣህ አትገሥጸኝ፤ በመዓትህም አትቅጣኝ።
ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች ስለ ስምንተኛ፥ የዳዊት መዝሙር።
እግዚአብሔር ሆይ! በቊጣህ አትገሥጸኝ፤ በመዓትህም አትቅጣኝ።
ዘካርያስ፥ አዝኤል፥ ሰሚራሞት፥ ኢያሔል፥ ዑኒ፥ ኤልያብ፥ መዕሤያ፥ በናያስ በመሰንቆ በልዑል ቃል ያዜሙ ነበር።
ማታትያስ፥ ኤልፋላይ፥ ሜቄድያስ፥ አብዴዶም፥ ይዒኤል፥ ዖዝያስም ስምንት አውታር ባለው በገና ይዘምሩ ነበር።
ዓይኖችን ክፈት፥ ከሕግህም ድንቅ ነገርን አያለሁ።
አቤቱ፥ እስከ መቼ ፈጽመህ ትረሳኛለህ? እስከ መቼስ ፊትህን ከእኔ ትመልሳለህ?
በዚያን ጊዜ በቍጣው ይናገራቸዋል፥ በመዓቱም ያውካቸዋል።
“በአንደበቴ እንዳልስት አፌን እጠብቃለሁ፤ ኃጥኣን በፊቴ በተቃወሙኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ” አልሁ፤
እግዚአብሔርን በጠራሁት ጊዜ ጽድቄን ሰማኝ፥ ከጭንቀቴም አሰፋልኝ፤ ይቅር አለኝ፥ ጸሎቴንም ሰማኝ።
ከኖኅ ዘመን ውኃ ጀምሮ ይህ ለእኔ ምስክር ነው፤ ቀድሞ ከእንግዲህ ወዲህ ምድርን እንዳልቈጣት እንደ ማልሁ፥
“መንፈስ ከእኔ ይወጣልና፥ የሁሉንም ነፍስ ፈጥሬአለሁና ለዘለዓለም አልቀስፋችሁም፤ ሁልጊዜም አልቈጣችሁም።
አቤቱ! ቅጣን፤ ነገር ግን ፈጽመህ እንዳታጠፋን በፍርድህ ይሁን እንጂ በቍጣህ አይሁን።
አንተ ባሪያዬ ያዕቆብ ሆይ! እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፥” ይላል እግዚአብሔር፤ አንተንም ያሳደድሁባቸውን አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁና፥ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፤ በመጠን እቀጣሃለሁ፥ ያለ ቅጣትም አልተውህም።”