ከዐመፅ አድራጊዎች ታደገኝ፥ ከደም ሰዎችም አድነኝ።
የለም፤ በልባችሁ ክፋትን ታውጠነጥናላችሁ፤ በእጃችሁም ዐመፅን በምድር ላይ ትጐነጕናላችሁ።
በእውነት ጽድቅን ትናገራላችሁን፥ ገዢዎች ሆይ፥ በቅን ትፈርዳላችሁን?
አይደለም! በልባችሁ ክፉ ነገርን ታቅዳላችሁ፤ በምድር ላይ የምትፈጽሙትም ሁሉ የዐመፅ ሥራ ነው።
ልጨነቅ ቀርቤአለሁና፥ የሚረዳኝም የለምና ከእኔ አትራቅ።
አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው? አቤቱ፥ ዝም አትበል፥ ቸልም አትበል።
ደግሞም ከፀሐይ በታች በጻድቅ ስፍራ ኃጥእ፥ በኃጥእም ስፍራ ጻድቅ እንዳለ አየሁ።
ክፉንም ጽሕፈት ለሚጽፉ ወዮላቸው!
የጻድቃን መንገድ የቀና ትሆናለች፤ የቅኖችም መንገድ ትጠረጋለች።
በአንቺ ውስጥ ደምን ያፈስሱ ዘንድ መማለጃን ተቀበሉ፤ በአንቺም አራጣና ትርፍ ወስደዋል፤ ቀማኛነትሽንና ኀጢአትሽን ፈጸምሽ፤ እኔንም ረሳሽኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
በውስጥዋ ያሉ አለቆችዋ የስስትን ትርፍ ለማግኘት ሲሉ ደምን ያፈስሱ ዘንድ፥ ነፍሶችንም ያጠፉ ዘንድ እንደሚናጠቁ ተኵላዎች ናቸው።
አሁንም የሚታበዩትን ሰዎች ብፁዓን ብለን እንጠራቸዋለን፣ ክፉንም የሚሠሩ ጸንተዋል እግዚአብሔርንም ይፈታተናሉ፥ ያመልጣሉም ብላችኋል።