እንደሚቀልጥ ሰም ያልቃሉ፤ እሳት ወደቀች፥ ፀሐይንም አላየኋትም።
ነፍሴ ሆይ፤ ንቂ! በገናና መሰንቆም ተነሡ! እኔም ማልጄ እነሣለሁ።
ልቤ ጽኑ ነው፥ አቤቱ፥ ልቤ ጽኑ ነው፥ እቀኛለሁ፥ እዘምራለሁ።
ነፍሴ ሆይ! ተነሺ፤ በገናዬና መሰንቆዬም ተነሡ! እኔም በማለዳ እነሣለሁ።
በበገናና በመሰንቆ፥ በመለከትም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ እግዚአብሔር ቤት ገቡ።
በመለከት ድምፅ አመስግኑት፤ በበገናና በመሰንቆ አመስግኑት፤
ከሚያጐሳቍሉኝ ኃጥኣን ፊት፥ ጠላቶቼ ግን ነፍሴን ተመለከትዋት፤
የልመናዬን ቃል ሰምቶኛልና እግዚአብሔር ይመስገን።
እንደ ሞተ ሰው ከልብ ረሱኝ፥ እንደ ጠፋ ዕቃም ሆንሁ።
አምላኬና ንጉሤ አንተ ነህ፤ ለያዕቆብ መድኀኒትን ያዘዝህ።
ጽዮን ሆይ፥ ተነሺ፥ ተነሺ፤ ጽዮን ሆይ፥ ኀይልሽን ልበሺ፤ አንቺም ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ያልተገረዘና ርኩስ ከእንግዲህ ወዲህ ወደ አንቺ አያልፍምና ክብርሽን ልበሺ።
የኢየሩሳሌም ፍርስራሾች ደስ ይበላቸው፤ እግዚአብሔር ይቅር ብሎ ኢየሩሳሌምን አድኖአታልና።
ስለዚህ ልቤን ደስ አለው፤ አንደበቴም ሐሤት አደረገ፤ ሥጋዬም ደግሞ በተስፋው አደረ።
ተነሺ፥ ዲቦራ ሆይ፦ ተነሺ፤ አእላፍን ከሕዝብ ጋር አስነሺ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ቅኔውንም ተቀኚ፤ ባርቅ ሆይ! በኀይል ተነሣ፤ ዲቦራም ባርቅን አጽኚው፥ የአቢኒሔም ልጅ ባርቅም ሆይ! ምርኮህን ማርክ።