በርሬ ዐርፍ ዘንድ እንደ ርግብ ክንፍን ማን በሰጠኝ አልሁ፥
በበጎ ፈቃድ መሥዋዕት እሠዋልሃለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ መልካም ነውና፣ ለስምህ ምስጋና አቀርባለሁ፤
እነሆ፥ እግዚአብሔር ይረዳኛል፥ ጌታም ለሕይወቴ ደጋፊ ነው።
መሥዋዕትህን በፍላጎቴ አቀርብልሃለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፥ ተገቢ ስለ ሆነ ለስምህ ምስጋና አቀርባለሁ
አቤቱ፥ የጽድቅህን ፍርድ ስማር በቅን ልብ አመሰግንሃለሁ።
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ እግዚአብሔርን አመስግኚ፥
ለመንጠቅ እንደሚያሸምቅ አንበሳ በላዬ አፋቸውን ከፈቱ።
የመድኀኒቴ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ ከደም አድነኝ፥ አንደበቴም በአንተ ጽድቅ ደስ ይለዋል።
እግዚአብሔርን እንደ ጽድቁ መጠን አመሰግናለሁ፥ ለልዑል እግዚአብሔርም ስም እዘምራለሁ።
እግዚአብሔር ነገሠ፥ ክብሩንም ለበሰ፤ እግዚአብሔር ኀይልን ለበሰ፥ ታጠቀም፤ ዓለምንም እንዳትናወጥ አጸናት።
ጌታ እግዚአብሔር ረዳኝ፤ ስለዚህም አላፈርሁም፤ ፊቴንም እንደ ባልጩት ድንጋይ አድርጌዋለሁ፤ እንዳላፍርም አውቃለሁ።
እነሆ፥ ጌታ እግዚአብሔር ይረዳኛል፤ ማን ይጎዳኛል? እነሆ፥ ሁላችሁ እንደ ልብስ ታረጃላችሁ፤ ብልም ይበላችኋል።