እንደ በጎች ሞት በሲኦል ይጠብቃቸዋል፥ ቅኖችም በማለዳ ይገዙአቸዋል፥ ረድኤታቸውም ከክብራቸው ተለይታ በሲኦል ትጠፋለች።
መዝሙር 50:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ በደሌን አውቃለሁና፥ ኀጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላካችን ይመጣል፤ ዝምም አይልም፤ የሚባላ እሳት በፊቱ፣ የሚያስፈራ ዐውሎ ነፋስም በዙሪያው አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም፥ እሳት በፊቱ ይቃጠላል፥ በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ ነፋስ አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላካችን ይመጣል፤ ዝም አይልም፤ የሚያቃጥል እሳት በፊቱ ነው፤ ኀይለኛ ዐውሎ ነፋስም በዙሪያው ነው። |
እንደ በጎች ሞት በሲኦል ይጠብቃቸዋል፥ ቅኖችም በማለዳ ይገዙአቸዋል፥ ረድኤታቸውም ከክብራቸው ተለይታ በሲኦል ትጠፋለች።
እግዚአብሔርም በእሳት ስለ ወረደበት የሲና ተራራ ሁሉ እንደ ምድጃ ጢስ ይጤስ ነበር፤ ከእርሱም እንደ እቶን ጢስ ያለ ጢስ ይወጣ ነበር፤ ተራራውም ሁሉ እጅግ ይናወጥ ነበር፤ ሕዝቡም ፈጽመው ደነገጡ።
እናንተ አእምሮ የሌላችሁ፥ ልቡናችሁን አረጋጉ፤ ጽኑ፤ አትፍሩ፤ እነሆ፥ አምላካችን ፍርድን ይመልሳል፤ ይበቀላልም፤ እርሱም መጥቶ ያድነናል።
እኔም አየሁ፤ እነሆም ከሰሜን በኩል ዐውሎ ነፋስና ታላቅ ደመና፥ የሚበርቅም እሳት መጣ፤ በዙሪያውም ፀዳል ነበረ፤ በመካከልም በእሳቱ ውስጥ የሚብለጨለጭ ነገር ነበረ።
እነሆ፥ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድድ ቀን ይመጣል፣ ትዕቢተኞችና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፣ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል፥ ሥርንና ቅርንጫፍንም አይተውላቸውም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
አምላክህም እግዚአብሔር በፊትህ እንዲያልፍ ዛሬ ዕወቅ፤ እርሱ የሚበላ እሳት ነው፤ እርሱ ያጠፋቸዋል፤ በፊትህም ያዋርዳቸዋል፤ እግዚአብሔርም እንደ ነገረህ ከፊትህ ያርቃቸዋል፥ ፈጥኖም ያጠፋቸዋል።
እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንለው እንዴት እናመልጣለን? ይህ በጌታ በመጀመሪያ የተነገረ ነበረና የሰሙትም ለእኛ አጸኑት።